በኦሮሚያ ክልል የሰሜን ሸዋ ዞን የገርበ ጉራቻ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ለ2019 በጀት ዓመት የከተማ ኮሪደር ልማት ስራን (G3 እና በላይ ኮንትራክተሮች) በጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ያወጣው ማስታወቂያ።
በኦሮሚያ ክልል የሰሜን ሸዋ ዞን የገርበ ጉራቻ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት
የመካከለኛ ኦሮሚያ ዞን የገርበ ጉራቻ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት የከተማ ኮሪደር ለማሰራት የተዘጋጀ የጨረታ ሰነድ
ሀ. የተወዳደሪዎች መመሪያ
- በዚሁ ዘርፍ የንግድ ፍቃድ ያለው የ2018/2019 የታደሰ የንግድ ፍቃድ የዘመኑን ግብር የከፈለ እና በኮንስትራክሽን ዘርፍ ተሰማርተው ለመገኘታቸው ዝርዝር የተመዘገቡበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችል እና በኮንስትራክሽን ዘርፍ በሙያው G3 እና ከዚያ በላይ ያላቸው መሆን አለባቸው።
- ተጫራቾች ዝርዝር የጨረታ ሰነድ የያዘ ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 22ኛው ቀን በስራ ሰዓት እስከ 6:30 ድረስ ብቻ የማይመለስ ብር 2000 (ሁለት ሺህ ብር) በሲንቄ ባንክ አካውንት ቁጥር 1055210501213 በመክፈል የባንክ ስሊፕ በማምጣትና ከገቢዎች በማሳረድ ከገርበ ጉራቻ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 1 ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ በፖስታ በማሸግ ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 21 የስራ ቀናት በ22ኛው ቀን እስከ 8:00 ሰዓት የጨረታ ማስከበሪያ ብር 100,000 /አንድ መቶ ሺህ/ ብር ወይም ሲፒኦ በማስያዝ ለዚሁ በተዘጋጀው ሣጥን ያስገባሉ።
- ሰዓቱን አሳልፎ የቀረበ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም።
- ጨረታው በ22ኛው ቀን በ8:30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በገርበ ጉራቻ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት ይከፈታል። ተጫራቾች ባይገኙም ጨረታውን ከመክፈት አያግደውም።
- ተጫራቾች ከማንኛውም ሙስና እና የብክነት ድርጊቶች ነፃ ለመሆናቸው በፌዴራል እና በክልል የወጡትን የግዥ ደንቦች የሚያከብር ስለመሆኑ ሰነድ ውስጥ የቀረቡትን ግዴታዎች አምኖበት መፈጸም ይኖርባቸዋል።
- ማንኛውም ተጫራች ጨረታውን በሕገወጥ መንገድ እንዲካሄድ የሞከረ ከጨረታ ውጪ ከመሆኑም በላይ ለወደፊቱም በሚካሄዱት ጨረታዎች እንዳይሳተፍ ተደርጎ ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ ለመ/ቤቱ ገቢ ይሆናል።
- ተጫራቾች ለሙያቸው ማረጋገጫ የስራ ልምድ እና የምስጋና ደብዳቤ ቢያቀርቡ ይመረጣል።
- መ/ቤቱ ሌላ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0920762750 /0910285005/ በመደወል መጠየቅ ይቻላል።
በኦ/ብ/ክልላዊ መንግስት መ/በ/ሸዋ ዞን የገበር ጉራቻ ከተማ አስ/ገንዘብ ጽ/ቤት
Summary
Gerbe Guracha Town Finance Office (North Shewa, Oromia) seeks contractors for the town corridor development works. Construction contractors of grade G3 and above with a renewed 2018/2019 licence and paid taxes may bid.
