የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንገዶች ባለሥልጣን ለዋናው መ/ቤትና በስሩ ላሉ ዲስትሪክቶች አገልግሎት የሚውሉ የደህንነት ካሜራዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለማስገጠም ያወጣው ማስታወቂያ (ቁጥር ማ/ኢ/መ/ባ/ኤሌ/05/19)።
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንገዶች ባለስልጣን
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ማ/ኢ/መ/ባ/ኤሌ/05/19
መ/ቤታችን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንገዶች ባለሥልጣን ለዋናው መ/ቤት እና በስሩ ላሉት ዲስትሪክቶች አገልግሎት የሚውል የደህንነት ካሜራዎች ብቁ ተጫራቾችን አወዳድሮ ማስገጠም ይፈልጋል።
በመሆኑም፤
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የሚያስችላቸውን የዘመኑን ግብር የተከፈለበትን ከሚፈለገው አገልግሎት ጋር የተዛመደ የንግድ ሥራ ወይም አገልግሎት ሥራ ፈቃድ፣ የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት ፣የመንግስት መሥሪያ ቤቶች በሚያወጡት ጨረታ ላይ መሳተፍ የሚያስችል የምስክር ወረቀት፣የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የፋይናንሻል ፕሮፖዛል አንድ ዋና እና ኮፒ እንዲሁም ቴክኒካል ፕሮፖዛሉን አንድ ዋና እና ኮፒ በተለያየ ፖስታ በማድረግ ኦሪጂናል እና ኮፒ በማለት እና የጨረታ ማስከበርያውን በተለየ ፖስታ በማሸግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ) ብቻ በመክፈል በባለሥልጣኑ ዋና መ/ቤት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኬዝ ቲም ቢሮ በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ።
- የጨረታው አሸናፊ የሚወሰነው በጨረታ ሰነዱ ውስጥ በተመለከቱት መስፈርቶች መሰረት ሲሆን ጨረታው ዜግነትን ሳይመለከት ለማንኛውም አቅራቢ ክፍት ነው።
- አቅራቢዎች ጨረታውን ገቢ የሚያደርጉት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን ከቀኑ 8:00 ሰዓት ድረስ ይሆናል። ጨረታው በዚያው ቀን ከቀኑ 8:30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ዕለቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሠዓት ይሆናል።
- ተጫራቾች በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ዕውቅና ካላቸው የፋይናንስ ተቋም በቅድመ ሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም ሲፒኦ (CPO) ለአንድ ማሽን ብር 300,000.00(ሦስት መቶ ሺህ) ብቻ በማሰራት ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር በማያያዝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። በኢንሹራንስ ዋስትና የሚቀርብ የጨረታ ማስከበሪያ ተቀባይነት የለውም።
- ተጫራቾች በጨረታው ደንብና መመሪያ መሰረት ጨረታውን ማቅረብ አለባቸው። ከጨረታው ደንብና መመሪያ ውጪ የሚቀርብ ማንኛውም የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም።
- መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ለበለጠ መረጃ የሚከተለውን አድራሻ መጠቀም ይችላሉ። የማዕከላዊ ኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን ግዥና ንብረት አስተዳደር ኬዝ ቲም ስልክ ቁጥር 0113659932 ወልቂጤ ኢትዮጵያ
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንገዶች ባለሥልጣን
Summary
Central Ethiopia Region Roads Authority seeks suppliers to supply and install security cameras for its head office and district offices. Open to any supplier regardless of nationality with a relevant licence, supplier registration and VAT certificate.
