Tender Detail

Tender Details

  • Company የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ግብርና ቢሮ
  • Address ዲላ ከተማ ፡ ደቡብ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 046-131-0134
  • Website
  • Deadline19 Dec 2026, 10:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • CountryEthiopia
  • Bid Document Priceብር 300 (የማይመለስ)
  • Bid Securityብር 80,000 (CPO ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና)
  • opening dateበዕለቱ 4:05
  • Sector Solar And Photovoltaic

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ግብርና ቢሮ የሶላር ግዥና ተከላ

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ግብርና ቢሮ


የሶላር ግዥ ከነተከላው ግዥ ጨረታ ማስታወቂያ 130/19

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ግብርና ቢሮ በISVCD ፕሮጀክት በጀት ድጋፍ የሶላር ግዥ ከነ-ተከላው በግልጽ ጨረታ ከዚህ በታች በሰንጠረዥ በተገለጸው መሰረት በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

ተ.ቁየዕቃው አይነትመለኪያብዛትየጨረታ ማስከበሪያየሚከፈትበት ሰዓትሰነዱ የሚገኝበት ቦታ
1የሶላር ግዥ ከነ-ተከላውበቁጥር180,000በ31ኛው ቀን በ4:00 ታሽጎ በዕለቱ 4:05 ይከፈታልደ/ኢ/ግ/ቢሮ ዲላ መምህራን ኮሌጅ ግቢ
  • በግዥ ስራ ዘርፉ የታደሰ ፍቃድ ፤የዘመኑን ግብር አጠናቀው የከፈሉ፤ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያለው፣ በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ ስለመመዝገባቸውና የቫት ተመዝጋቢነት ማስረጃዎች ያላቸውና የሚያቀርቡ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ።
  • ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ለ60 ቀናት የፀና መሆን ይኖርበታል።
  • በተጫራቾች የሚቀርበው የጨረታ ማስከበሪያ ሲ-ፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ያሲያዙበትን ማቅረብ አለባቸው።
  • ተጫራቾች በቢሮ የተዘጋጀውን መደበኛ የጨረታ ሰነድ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ ቀናት እስከ 30ኛ ቀን 11:30 ድረስ የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል በዲላ ከተማ መምህራን ኮሌጅ ግቢ ውስጥ ከሚገኘው የግብርና ቢሮ ግዥ ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት ክፍል መውሰድ ይችላሉ።
  • ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነድ በመሙላት ቴክኒካል ሰነድ አንድ ኦርጂናል እና ሁለት ኮፒ እንዲሁም ፋይናንሻል ሰነድ አንድ ኦርጂናል እና ሁለት ኮፒ አዘጋጅቶ በማሸግና ሁሉንም በአንድ እናት ፖስታ በማሸግ በ31ኛው ቀን 4:00 ሰዓት በቢሮው ግዥ ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት ለዚሁ ጨረታ ተብሎ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይቻላል። እንዲሁም የጨረታው ሳጥን በ4:00 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ 4:05 ተጫራቾች (ተወካዮቻቸው) በተገኙበት በቢሮው የግዥ ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት ክፍል ይከፈታል።
  • ቢሮው በቀረበው ጨረታ ላይ ካሸናፊው ድርጅት ጋር ውል ከመፈራረሙ በፊት የግዥውን 20% ፐርሰንት መቀነስ ወይም መጨመር ይችላል።
  • የጨረታው መክፈቻ ቀን ማለትም 31ኛው ቀን የመንግስት የስራ ቀን ካልሆነ ጨረታው በቀጣይ ባለው የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓትና ቦታ የሚከፈት ይሆናል።
  • ከ200,000 ሺህ በላይ ለሆኑት ግዥዎች ተጫራቾች ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው።
  • ከአንድ በላይ የሆኑ ተወዳዳሪዎች ያቀረቡት ዋጋ እኩል በሚሆንበት ወቅት በእጣ የሚለይ ይሆናል።
  • ቢሮው ለዚሁ ጨረታ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ 046-131-0134 ይጠቀሙ።

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ግብርና ቢሮ

Summary
South Ethiopia Region Bureau of Agriculture invites suppliers to provide and install a solar system under the ISVCD project budget. Technical and financial offers in separate sealed envelopes.
Save Tender