የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል የቤንች ሸኮ ዞን የሸኮ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ለ2019 በጀት ዓመት የግ/መሬት ማዘጋጃ ቤት የቢሮ ግንባታ ስራን (ደረጃ 5 GC/BC እና በላይ) በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ያወጣው ማስታወቂያ።
በደ/ምዕ/ኢ/ህ/ክ/መ የቤንች ሸኮ ዞን የሸኮ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
በ/ደ/ምዕ/ኢ/ህ/ክ/መ የቤንች ሸኮ ዞን የሸኮ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ለ2019 በጀት ዓመት የግ/መሬት ማዘጋጃ ቤት የቢሮ ግንባታ ስራ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማስገንባት ይፈልጋል። ስለዚህ የሚከተሉትን የጨረታ መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቶች/ድርጅቶች እንዲወዳደሩ ይጋብዛሉ።
- ደረጃ 5 GC BC እና ከዚያ በላይ የሆኑ
- ተጫራቾች ለመወዳደር የሚያስችል በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የስራ ንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን የንግድ ፍቃዳቸውን ያሳደሱ፣
- የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ፣
- የታደሰ ብቃት ማረጋገጫ በተገቢው ሁኔታ ማቅረብ የሚችሉ፣
- የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ተመዝጋቢ የሆኑትን የምዝገባ ሰርተፊኬት ኮፒውን ማቅረብ የሚችሉ፣
- በአቅራቢነት የተመዘገቡበት የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
- የጨረታ ማስከበሪያ ብር 300,000 (ሶስት መቶ ሺህ ብር) ብቻ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ፣ በሌተር ኦፍ ክሬዲት ከጨረታ ሰነድ ጋር በፖስታ ለብቻው በማሸግ ማቅረብ የሚችሉ።
- የጨረታ ሰነዱን ብር 1000 (አንድ ሺህ ብር) ብቻ በመክፈል መግዛት ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የገዙት ሰነድ (ፋይናንሻል እና ቴክኒካል) ከላይ የተዘረዘሩትን አስፈላጊ የሆኑትን መረጃዎች አንድ ኦርጂናል እና 2 ኮፒ እያንዳንዱ ለብቻ በሰም በማሸግ ፣ በመፈረም እና በጥቅል በሰም በታሸገ ፖስታ ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች እያንዳንዱ ፖስታ በሰም ታሽጎ ማህተም በመምታት ሙሉ አድራሻ በመፃፍ እና በመፈረም ኦርጂናል እና ኮፒ የሚል ፅሁፍ በግልፅ በሚታይ ቦታ ላይ መፃፍ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች በሁሉም የዋጋ ማቅረቢያ ሰነዶች ላይ የተጫራቾች ህጋዊ ወኪል ፊርማ እንዲሁም የድርጅቱ ማህተም መኖር አለበት።
- ተጫራቾች እያንዳንዱ ፖስታ የሚወዳደሩበትን የስራ ቦታ፣ የተቋራጩ አድራሻ እና የተወካዩ ስልክ ቁጥር በመግለፅ መፃፍ አለባቸው።
- ተጫራቾች ጨረታው በማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ21 ተከታታይ የሥራ ቀናት ክፍት ሆኖ በ22ኛው ቀን 4:30 ሰዓት ታሽጎ በ22ኛው ቀን 8:30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ቀኑ በዓል ወይም ዝግ ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን ጨረታው ይከፈታል።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- አቅራቢዎች የሚሞሉት ዋጋ ከነቫት መሆን አለበት ካልሆነ መ/ቤቱ የተሞላውን ዋጋ ከነቫቱ እንደተሞላ አድርጉ ነው የሚወስደው
- ይህ ጨረታ ለ60 /ስልሳ/ ቀናት ፀንቶ የሚቆይ ይሆናል።
አድራሻ - ቤንች ሸኮ ዞን ሸኮ ወረዳ ፋይ/ኢኮ/ልማ/ጽ/ቤት ስልክ ቁጥር 0930573008 ይደውሉ
በ/ደ/ምዕ/ኢ/ህ/ክ/መ የቤንች ሸኮ ዞን የሸኮ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት
Summary
Sheko Woreda Finance and Economic Development Office (Bench Sheko Zone) seeks a contractor to build an office for the town municipality. Grade 5 GC/BC and above with renewed licence, competence certificate, TIN, VAT and supplier registration may bid.
