የኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ ለፋብሪካው አገልግሎት የሚውል 13,000,000 የሲሚንቶ ማሸጊያ ከረጢት (Laminated Poly-Propylene Bags) በሀገር ውስጥ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ያወጣው ማስታወቂያ (ቁጥር ሙሲፋ/13/2019)።
Chemical Industry Corporation Mugher Cement Factory (በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ)
የሀገር ውስጥ ግልፅ ጨረታ
ቁጥር ሙሲፋ/13/2019
በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ አገልግሎት የሚውል የሲሚንቶ ማሸጊያ ከረጢት (Laminated Poly-Propylene Bags) ብዛቱ 13,000,000 በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ የታደሰ የንግድ ፍቃድ እና የንግድ ምዝገባ ያላቸው የ2018/2019 ዓ.ም ተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፊኬት የታክስ ከፋይ ምዝገባ ኮፒ በመያዝ ተጫራቾች የማይመለስ ብር 575.00 ተጨማሪ እሴት ታክስን ጨምሮ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን አዲስ አበባ በኮርፖሬሽን ዋና መ/ቤት ገርጂ የቀድሞው ኤምፔሪያል ህንፃ ከሚገኘው የፋብሪካው የግዥ መምሪያ ቢሮ እየቀረቡ መግዛት ይችላሉ። ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 2,000,000.00 (ሁለት ሚሊዮን ብር) በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ (Chemical Industry Corporation Mugher Cement Factory) ስም የተዘጋጀ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ (C.P.O) ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ ባንክ ጋራንቲ ከቴክኒክ ዶክመንቶቹ ጋር በማያያዝ ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ታህሳስ 6 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 3:30 ሰዓት ድረስ በሰም በታሸገ ኤንቬሎፕ የጨረታ ሰነዳቸውን አዲስ አበባ በኮርፖሬሽን ዋና መ/ቤት ገርጂ የቀድሞው ኤምፔሪያል ህንፃ ከሚገኘው የፋብሪካው የግዥ መምሪያ ቢሮ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
ጨረታው በዕለቱ ታህሳስ 6 ቀን 2019 ዓ.ም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት በግዥ መምሪያ ቢሮ ይከፈታል።
ፋብሪካው ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አዲስ አበባ
