Tender Detail

Tender Details

  • Company የወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ፕላን ልማት መምሪያ
  • Address , Phone: 0461800863
  • Website
  • Deadline01 Dec 2026, 10:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • CountryEthiopia
  • Bid Document Priceብር 1000.00 (የማይመለስ)
  • Bid Securityሎት-17 ብር 100,000.00፤ ሎት-18 ብር 50,000.00 (CPO)
  • opening dateበዕለቱ ከቀኑ 4:30
  • Categories Maintenance And Repair , Vehicle Spare Parts

በደቡብ ኢት/ያ ክልል የወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ፕላን ልማት መምሪያ ለ2019 በጀት ዓመት የተለያዩ የተሽከርካሪ ጥገና እና መለዋወጫ ዕቃ ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

የወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ፕላን ልማት መምሪያ


ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

በደቡብ ኢት/ያ ክልል የወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ፕላን ልማት መምሪያ ለ2019 በጀት ዓመት የተለያዩ የተሽከርካሪ ጥገና እና መለዋወጫ ዕቃ ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

  1. ሎት-17 የመኪና ጥገና እና መለዋወጫ ዕቃ ግዥ ሎት-18 ሞተር ጥገና እና መለዋወጫ ዕቃ ግዥ ጨረታውን ለመሳተፍ የሚፈልጉት:-
  2. በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉት በሚመለከታቸው መስሪያ ቤቶች በአቅራቢነት የተመዘገቡና ለ2019 በጀት ዓመት በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ ቫት ተመዝጋቢ የሆኑ፣ የአቅራቢነት ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉና በ EGP የተመዘገቡ፣ ከዚህ በፊት ላከናወናቸዉ ተመሳሳይ ሥራዎች አገልግሎቶች ከአሠሪዉ አካል የመልካም ሥራ አፈጻጸም ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መወዳደር ይችላሉ።
  3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከታወጀበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት (አስራ አምስት ቀናት) ከታች ከተጠቀሰው አድራሻ መግዛት ይችላሉ።
  4. የተዘጋጀውን መደበኛ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 1000.00 (አንድ ሺህ ብር) በማቅረብ መግዛት ይችላሉ። የጨረታ ሰነድ የሚገኝበት ቦታ ወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ፕላን ልማት መምሪያ ግዥ ንብረት አስተዳደር ዋና ሥራ ሂደት ቢሮ ይገኛል።
  5. ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን አንስቶ እስከ 16ኛዉ ቀን ከቀኑ 4:00 (አራት ሰዓት) ድረስ ለጨረታዉ በተዘጋጀዉ ሳጥን ውስጥ የጨረታ ሰነድ ማስገባት ይችላሉ። ዘግይቶ የሚቀርብ ጨረታ ተቀባይነት አይኖረውም ሳይከፈት ለተጫራቹ ይመለስለታል።
  6. ጨረታው የሚከፈተው ሁሉም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸውና ሌሎች መገኘት የሚፈልጉ ባሉበት በ16ኛው ቀን ከቀኑ 4:00 ላይ ታሽጎ በዕለቱ ከቀኑ 4:30 የሚከፈት ይሆናል። 16ኛው ቀን የበአላት ቀን ከሆነ (የሥራ ቀን ካልሆነ) በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል።
  7. ተጫራቾች የጨረታ ዋስትና ለየመኪና ጥገና እና መለዋወጫ ዕቃ ግዥ 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር) እና ለሞተር ጥገና እና መለዋወጫ ዕቃ ግዥ 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር) በባንክ የተመሰከረለት ሲፒኦ (CPO) ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  8. ርክብክብ የሚፈጸምበት ቦታ ወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳዳር ፋይናንስና ፕላን ልማት መምሪያ ቅጥር ግቢ ዉስጥ ይሆናል።
  9. የወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ፕላን ልማት መምሪያ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ 0461800863 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ።

የወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ፕላን ልማት መምሪያ

✨ messages.ai_summary
Wolaita Sodo City Administration Finance and Plan Development Department seeks bidders for vehicle repair and spare parts (lot 17) and engine repair and spare parts (lot 18). Open bid; EGP registration required.
Save Tender

Procurement of Spare Parts

READ MORE
Procurement of Spare Parts

READ MORE