Tender Detail

Tender Details


የኢትዮጵያ ማረሚያ ኮሌጅ ለ2019በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውል ስፖርት ቱታ ቶርሽን ጫማ፤ የተለያዩ ሲቪል አልባሳት እና የተለያዩ የመጽሐፍት ህትመት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

የኢትዮጵያ ማረሚያ ኮሌጅ


የጨረታ ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ ማረሚያ ኮሌጅ ለ2019በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውል ስፖርት ቱታ ቶርሽን ጫማ፤ የተለያዩ ሲቪል አልባሳት እና የተለያዩ የመጽሐፍት ህትመት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ከሥራው ጋር የተገናኘ በዘመኑ የታደሠ የንግድ ፍቃድ፤ የዘመኑን ግብር ለመከፈላቸው የሀገር ውስጥ የድጋፍ ደብዳቤ ከገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚ/ር የሚሰጠውን የምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሠርተፊኬትና ሌሎች ተጨማሪ መረጃዎች ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።

ተጫራቾች የጨረታ መመሪያና የዕቃ ዝርዝር መግለጫ የሆነውን የጨረታ ሠነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ ብር 100.00/አንድ መቶ ብር/ በመያዝ ዘወትር በስራ ሠዓት ከአ/አበባ በደብረብርሃን መስመር 63 ኪ/ሜትር ርቀት ላይ በስተቀኝ በኩል በሚገኘው የኢትዮጵያ ማረሚያ ኮሌጅ ሂሳብና በጀት ቢሮ ቁጥር 12 በመምጣት መግዛት የምትችሉ ሲሆን፦

ተ.ቁ የእቃው ዓይነት ጨረታው የሚከፈትበት ቀንና ሰዓት
1 ስፖርት ቱታ ቶርሽን ጫማ፣ የተለያዩ ሲቪል አልባሳት የተለያዩ የኤሌክትሪክ እቃዎች እና የተለያዩ የመጽሐፍት ህትመት ግዥ ህዳር 18/03/2019ዓ/ም ከቀኑ 8:00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን 8:30 ሰዓት ላይ ይከፈታል

ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ቀጥታ የሚሆን ሲፒኦ ብር 50,000.00/ሃምሳ ሺህ/ ብር ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ተረጋግጦ በሚሰጥ (CPO) በማሰራት የጨረታ መወዳደሪያ ፖስታ ውስጥ በማስገባት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።የሚቀርበው ጨረታ ሠነድ በሰም በታሸገ ፖስታ መሆን እንዳለበት መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ መሆኑን እናሳስባለን።

ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር:- 0116720000 እና 0920169144 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።

የኢትዮጵያ ማረሚያ ኮሌጅ

✨ messages.ai_summary
Ethiopian Correctional College seeks suppliers of sports tracksuits and shoes, civilian clothing, electrical items and printing of various books. Open bid.
Save Tender