ድርጅታችን አሰር ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግል ማህበር የተለያዩ ፕሮጀክቶችን በመገንባት ላይ ይገኛል። ለዚሁ አገልግሎት የሚውል ጥራቱን የጠበቀ አሸዋ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
አሰር ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግል ማህበር
የአሸዋ አቅርቦት ጨረታ ማስታወቂያ
ድርጅታችን አሰር ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግል ማህበር የተለያዩ ፕሮጀክቶችን በመገንባት ላይ ይገኛል። ለዚሁ አገልግሎት የሚውል ጥራቱን የጠበቀ አሸዋ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል። በመሆኑም ጥራቱን የጠበቀ አሸዋ ማቅረብ የምትችሉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች በማሟላት መጫረት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
- ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉበት ማስረጃ አያይዘው ማቅረብ የሚችሉ፣
- ተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ተመዝጋቢና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸው፣
- ጥራት ያለው አሸዋ በበቂ ሁኔታ ማቅረብ የሚችሉ
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን ዋናውንና ኮፒውን በታሸገ ኢንቨሎፕ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለተከታታይ 7 የሥራ ቀናት በዋናው መ/ቤት በሚገኘው ግዥ መምሪያ ብር 230.00 /ሁለት መቶ ሰላሣ ብር/ በመክፈል ሰነዱን መግዛትና ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች በሚያቀርቡት ሰነድ እና የፋይናንሻል ፕሮፖዛላቸው በሰም በታሸገ ፖስታ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፣
- ጨረታው ህዳር 10/2019 ዓ/ም ከቀኑ 9:00 ሰዓት ተዘግቶ በእለቱ ቀን 9:30 ላይ ተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፣
- ኩባንያው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ:-
- ፍላጎት ያላችሁ አመልካቾች ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከኢምፔሪያል አደባባይ ወደ መገናኛ በሚወስደው መንገድ ዲ ኤች ገዳ ቀለም ፋብሪካ ጀርባ ባለው ዋናው መ/ቤት ግዥ መምሪያ በመቅረብ የጨረታውን ሰነድ መግዛትም ሆነ ማስገባት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
- ስልክ ቁጥር :-0116-62-03-57 ወይም 0116-18-94-85
- ሞባይል 0912-100824
አሰር ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግል ማህበር
✨ messages.ai_summary
Aser Construction PLC seeks suppliers of quality sand for its various construction projects. Open bid.
Not stated in the notice: bid security. Check the original document or ask the issuer.
