በዋግ ኽምራ ዞን የሠቆጣ ወረዳ ፍርድ ቤት የG+0 ቢሮ ህንጻ ግንባታ
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በዋግ ኽምራ ዞን የሠቆጣ ወረዳ ፍርድ ቤት የግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን
ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ጨ-1/ 83/2019
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በዋግ ኽምራ ዞን የሠቆጣ ወረዳ ፍርድ ቤት የግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን በ2019 ዓ.ም በጀት አመት ከዚህ በታች የተገለጸውን የቢሮ ግንባታ በብሄራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማስገንባት ይፈልጋል::
ስለሆነም
1. ባለ G+0 ህንጻ ግንባታ በጠቅላላ እና ሕንፃ ስራ ተቋራጭ ከደረጃ 6 እና ከዚያ በላይ ያሉ ኮንትራክተሮችን አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል:: ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ይጋብዛል::
- ተጫራቾች በዘርፉ የ2019 ዓ/ም ህጋዊ ፍቃድ ያላቸው ያሳደሱና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ::
- የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር/TIN/ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ::
- የግዥ መጠናቸው ከብር 200000/ሁለት መቶ ሺ ብር /እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ከፋይ ለመሆናቸው የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ::
- በፌዴራል ደረጃ ካላቸው የምስክር ወረቀት በተጨማሪ በክልሉ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን የአጭር ግዜ ምዝገባ ሰርተፍኬት ያላቸው መሆን አለበት::
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር1-4 የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው ::
- የግንባታው አይነትና ዝርዝር መግለጫ/ስፔስፊኬሽን/ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ::
- ተጫራቾች ለህንፃ ግንባታ ሰነድ የማይመለስ ብር 500.00/አምስት መቶ ብር /በመክፈል ጨረታው በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ከፍርድ ቤት ድረስ በመገኘት ቢሮ ቁጥር 3 መግዛት ይችላሉ ::
- የግንባታው ጨረታ በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ለ20 /ሃያ/ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ ይውላል::
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት የግንባታ ጠቅላላ ዋጋ 2 % በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ/ CPO / ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በባንክ የተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ክሬዲት ወይም በሰቆጣ ወረዳ ፍርድ ቤት በመ/ሂ-1ገቢ አድርጎ ኮፒውን ከዋናው የጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ አለባቸው::
- ማንኛውም ተጫራቾች የህንጻ ግንባታ ስራ ፋይናንሻሉን እና ቴክኒካል መረጃዎችን በተለያየ ፖስታ በማሸግ በሰቆጣ ወረዳ ፍ/ቤት በግዥ/ን/አስ/ር ቡድን ቢሮ ቁጥር 3 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ለግንባታ ሥራን ከ03/03/2019 እስከ 22/03/2019ዓ/ም ጨረታው በአየር ላይ የሚቆይ ሲሆን ፤በተጨማሪም በጨረታ ሰነዱ ላይ ስማቸውን፣ፊርማቸውን፣ሙሉ አድራሻ፣የድርጅቱ ማህተም መሟላት ያለባቸው ሲሆን ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቀን23/03/2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 3:30 ሰዓት ታሽጎ በ4:00 ሰዓት ግዥ /ን/አስ/ር ቡድን ቢሮ ቁጥር 3 ይከፈታል::
- ተጫራቾች አሸናፊነታቸው ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በ5 ቀን ውስጥ የዋጋውን 10% በባንክ በተረጋገጠ/CPO /ወይም በጥሬ ገንዘብ /መ/ሂ-1 በማስያዝ ውል መፈረም አለባቸው::
- ተጫራቾች አሸናፊነታቸው ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በ5 ተከታታይ ስራ ቀናት ውስጥ የውል ማስከበሪ አስይዘው ውል ካልፈረሙ መ/ቤቱ የጨረታ ማስከበሪያውን የመውረስ መብት አለው::
- መ/ቤቱ ከላይ በተራ ቁጥር 1 ለቀረቡት የጨረታ ሰነድ ማንኛውም ህጋዊ ተወዳዳሪ የሚወዳደርባቸውን የጨረታ ሰነዶች በጨረታ ሰነዱ ላይ የቀረቡት የግንባታ አይነትና ዝርዝር መግለጫ/ስፔስፊኬሽን/ መሰረት የመሙላት ግዴታ አለባቸው::
- አሸናፊው የአሸነፈውን ግንባታ ከሚፈለግበት ቦታ ሰርቶ ለመ/ቤቱ በማስረከብ ሂሳቡን በስሙ የማወራረድ ግዴታ አለበት::
- በጨረታው ቅሬታ ያላቸው ተጫራቾች ጨረታው ከተከፈተና አሸናፊው ከተለየ በ5 የስራ ቀናት ውስጥ ባለው ቅሬታቸውን ለሚመለከታቸው አካል ማቅረብ አለባቸው::ከተጠቀሰው ቀን በኋላ የሚቀርብ አቤቱታ ተቀባይነት የለውም::
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 3 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0335403887 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ::
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
- ጨረታው ከተዘጋ በኋላ የሚቀርብ የመጫረቻ ሰነድ ተቀባይነት የለውም::
- የጨረታው መዝጊያ ጊዜ ከተጠናቀቀ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግና ከጨረታው እራሳቸውን ማግለል አይችሉም::
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በዋግ ኽምራ ዞን የሠቆጣ ወረዳ ፍርድ ቤት የግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን
Summary
Sekota Woreda Court in Wag Hemra Zone, Amhara, invites grade 6 and above GC/BC contractors to construct a G+0 office building. Open bid.
