Tender Detail

Tender Details

  • Company የሲዳማ መንገዶች ባለስልጣን (Sidama Roads Authority)
  • Address ሀዋሳ ከተማ ፡ ሲዳማ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0462128588
  • Website
  • Deadline22 Nov 2026, 12:00 PM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Priceብር 300.00 (የማይመለስ)
  • Bid Securityብር 150,000 (CPO ወይም Unconditional Bid Bond)
  • opening dateበዚሁ ቀን ከቀኑ 8:30 ሰዓት፣ በባለስልጣኑ መ/ቤት አደራሽ
  • Categories Construction Materials And Raw Materials

የሲዳማ መንገዶች ባለስልጣን በተለያዩ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቶች ላይ ለቱቦ ሥራ የሚሆን ሞልድ ከዚህ በታች በተገለጸው መሠረት መስፈርቱን የሚያሟሉ ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

የሲዳማ መንገዶች ባለስልጣን (Sidama Roads Authority)


በድጋሚ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የግዢ መለያ ቁጥር-ሲ/መ/ባ/003/2019

የሲዳማ መንገዶች ባለስልጣን በተለያዩ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቶች ላይ ለቱቦ ሥራ የሚሆን ሞልድ ከዚህ በታች በተገለጸው መሠረት መስፈርቱን የሚያሟሉ ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ተ.ቁ የእቃው አይነት ብዛት
1 ሞልድ 280 ሴሜትር 8
2 ሞልድ Ø90CM ሴሜትር 8
3 ሞልድ Ø1 ሜትር 8
4 ሞልድ Ø1.2 ሜትር 8

በዚሁ መሠረት:-

  1. የኮንስትራክሽን መሣሪያዎች አቅራቢነት ፍቃድ ያላቸው
  2. ተጫራቾች አግባብነት ያለው ለዘመኑ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሠርተፊኬት፤ የግብር ከፋይ ሰርተፊኬት እና በጨረታ መወዳደር የሚያስችል የዘመኑን ግብር የከፈለበትን ታክስ ክሊራንስ እንዲሁም ከመንግሥት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ መመዝገባቸውን የሚያሳይ ሰርተፊኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  3. ከሲዳማ መንገዶች ባለስልጣን ጋር ውለታ ገብቶ በአፈጻጸም ችግር ምክንያት ማስጠንቀቂያ የተሰጠው ሰነዱን መግዛትም ሆነ መወዳደር አይችልም::
  4. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 300,00 (ሦስት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10(አሰራ ተከታታይ ቀናት ከባለሥልጣኑ መ/ቤት ግዥ የፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮቁ ጥር 5 ቀርበው መግዛት ይችላሉ።
  5. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ - ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ(CPO) ወይም ከታወቀ ባንክ የቀረበ የጨረታ ማስከበሪያ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ ዋስትና (Unconditional Bid Bond) ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል በተጫራቾች የሚቀርበው የጨረታ ማስከበሪያ ከጠቅላላ ዋጋ 150,000/አንድ መቶ ሃምሳ ሺህ ብር ብቻ/ ማስያዝ ያለባቸው ሲሆን ተጫራቾች የሚያቀርቡት የጨረታ ማስከበሪያ መጠን ከላይ : በተገለጸው መሠረት ይሆናል። ከባንክ የሚቀርበው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (Bid Bond) ለ120 ቀናት ፀንቶ የሚቆይ መሆን ይኖርበታል።
  6. የጨረታ ሰነዱ በተጫራቾች መመርያ መሠረት ተሞልቶ ጨረታ ማስከበርያ Bid Security/ ፋይናሻል አንድ ዋና (ኦርጅናል) እና ሁለት ኮፒዎችን እንዲሁም ቴክኒካል አንድ ዋና (ኦርጅናል) እና ሁለት ኮፒ ሰነዶች በተለያየ ፖስታ በሰም በማሸግ ለየብቻቸው ታሽጎ በአንድ እናት ፖስታ ውስጥ ተካተውና በሁሉም ዶክመንት ላይ ስምና አድራሻ በመጻፍ ህጋዊ የሆነ ማህተም በመምታት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከጧቱ 3:00 እስከ 6:00 ሰዓት በሲዳማ መንገዶች ባለሥልጣን በግዥ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር - ዳይሬክቶሬት ክፍል ለዚሁ አገልግሎት በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። የጨረታ ማስከበሪያው ከቴክኒካል ሠነድ ጋር አብሮ መታሸግ አለበት:: ሆኖም የተጠቀሰው ቀን የእረፍት ወይም የህዝብ በዓል ቀን ሆኖ ከዋለ በቀጣይ በስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ላይ የሚከፈት ይሆናል::
  7. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወከሎቻቸው በተገኙበት ከላይ የጨረታ መክፈቻ ተብሎ በተጠቀሰው ቀንና ቦታ ከቀኑ 6:00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ ከቀኑ 8:30 ሰዓት ላይ በባለስልጣኑ መ/ቤት አደራሽ ይከፈታል።
  8. ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው:

ስልክ ቁጥር:- 0462-128-446

ሲዳማ መንገዶች ባለሥልጣን
ሀዋሳ

✨ messages.ai_summary
Sidama Roads Authority re-tenders the purchase of moulds for pipe work on its road construction projects: 8 each of four sizes (280 cm, Ø90 cm, Ø1 m and Ø1.2 m). Open bid.
Save Tender