Tender Detail

Tender Details

  • Company Tarcha polytechnic College (የታርጫ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ)
  • Address በዳውሮ ዞን ፡ ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: - - - -
  • Website
  • Deadline03 Dec 2026, 10:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • CountryEthiopia
  • Bid Document Priceብር 500.00
  • Bid Securityብር 100,000.00 (CPO)
  • opening dateበዕለቱ 4:30 ሰዓት
  • Categories Building Construction

በደ/ም/ኢ/ህ/ክ/መ/ በዳውሮ ዞን የታርጫ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በ2019 በጀት ዓመት ለሠልጣኞች ለመማሪያ አገልግሎት የሚውል G+2 ታሳቢ G+0 መንታ ህንፃ እየተሰራ ሳይጠናቀቅ ቆሞ የነበረው በጨረታ አወዳድሮ ለማስገንባት ይፈልጋል::

Tarcha polytechnic College (የታርጫ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ)


የጨረታ ማስታወቂያ

የግዥ/የጨረታ መለያ ቁጥር ታፖቴኮ/05/2019 ዓ.ም

በደ/ም/ኢ/ህ/ክ/መ/ በዳውሮ ዞን የታርጫ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በ2019 በጀት ዓመት ለሠልጣኞች ለመማሪያ አገልግሎት የሚውል G+2 ታሳቢ G+0 መንታ ህንፃ እየተሰራ ሳይጠናቀቅ ቆሞ የነበረው በጨረታ አወዳድሮ ለማስገንባት ይፈልጋል:: ስለዚህ የሚከተሉትን የጨረታ መስፈርቶችን የሚያሟሉ ተጫራቾች ሊወዳደሩ ይችላሉ::

  1. ህንጻ ሥራ ተቋራጭ ደረጃ 6 እና ጠቅላላ ሥራ ተቋራጭ ደረጃ 7 እና ከዚያ በላይ የሆኑ፣
  2. በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድና የአቅራቢዎች ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ አለበት፣
  3. የተጨማሪ እሴት ታክስ እና የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ሰርተፍኬት ማቅረብ አለበት፣
  4. የዘመኑ ግብር ስለመከፈሉ እና በጨረታ ይሳተፉ ደብዳቤን ከሚመለከተው አካል ማቅረብ አለበት፣
  5. የጨረታ ሰነድ 500.00/አምስት መቶ ብር ብቻ/በኮሌጃችን የንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር 1000042580647 ላይ ገቢ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከታወጀበት ቀን ጀምሮ ባሉት 21 ተከታታይ ቀናት ውስጥ በሥራ ሰዓት ቀርበው ከኮሌጃችን ግ/ን/አስ/ዳ/ት 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 02-16 ላይ ቀርበው መግዛት ይችላሉ፣
  6. ተጫራቾች በጨረታ ሰነድ ላይ ግልጽ በሆነ ስርዝ ድልዝ የሌለ በሚነበብ ጽሁፍ የድርጅቱን ስምና ፊርማ ማህተም፣ የስልክ ቁጥራቸውንና ዋጋ ሞልተው ማቅረብ አለበት፣
  7. የጨረታ ማስከበሪያ ብር 100,000.00/አንድ መቶ ሺህ ብር/ ብቻ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሲፒኦ (CPO) በኮሌጃችን ስም በማዘጋጀት ከቴክኒካል መረጃ ፖስታ ጋር አንድ ላይ አያይዞ ማቅረብ አለበት፣
  8. ተጫራቾች የቴክኒካል መረጃ ለየብቻ በፖስታ በማሸግ፣የፋይናንሻል መረጃ ኦሪጅናልና ሁለት የኦሪጅናል ኮፒ ለየብቻ አሽጎ በኮሌጃችን ግ/ን/አስ/ዳ/ት 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 02-16 ለዚሁ ዓላማ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ በሥራ ሰዓት ቀርበው መክተት አለበት፣
  9. የጨረታ ሣጥኑ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከታወጀበት ቀን ጀምሮ 21 ተከታታይ ቀናት ከተቆጠረ በኋላ በ22ኛው ቀን ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ 4:30 ሰዓት ላይ ይከፈታል:: ዕለቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የመንግሥት ሥራ ቀን ሆኖ ሰዓቱ እንደተጠበቀ ሲሆን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም የጨረታ አከፋፈት ሂደቱን አያስተጓጉልም፤
  10. አሸናፊ የሆነ የሆነ ተጫራች አሸናፊነቱ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ 7 የሥራ ቀናት ውስጥ የውል ማስከበሪያ ዋስትና በማስያዝ ከኮሌጁ ጋር ውል መግባት አለበት፣
  11. የጨረታ ማስታወቂያ የተጫራቾች መመሪያ ሆኖ ያገለግላል፣
  12. ኮሌጁ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

በዳውሮ ዞን የታርጫ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ

✨ messages.ai_summary
Tarcha Polytechnic College in Dawuro Zone, South West Ethiopia, invites building contractors grade 6 and general contractors grade 7 and above to complete a stalled G+2 twin classroom building for trainees. Open bid.
Save Tender