Tender Detail

Tender Details

  • Company የሲዳማ መንገዶች ባለስልጣን (Sidama Roads Authority)
  • Address ሀዋሳ ከተማ ፡ ሲዳማ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0462128588
  • Website
  • Deadline22 Nov 2026, 12:00 PM
  • magazineAddis Zemen
  • CountryEthiopia
  • Bid Document Priceብር 300 (የማይመለስ)
  • Bid Securityብር 100,000 (CPO ወይም ቅድመ ሁኔታ የሌለው የባንክ ዋስትና)
  • opening dateበዚሁ ቀን ከቀኑ 8:30 ሰዓት፣ በባለስልጣኑ መ/ቤት አደራሽ
  • Categories Vehicle Spare Parts

የሲዳማ መንገዶች ባለስልጣን ለ2019 በጀት ዓመት የተለያዩ መንገድ ለሚያስራቸው ማሽነሪዎች፤ከባድ መኪናዎች የሚውል ቮልቮ ሎቤድ መለዋወጫ ዕቃዎች ግዥ መስፈርቱን ከሚያሟሉ አቅራቢዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

የሲዳማ መንገዶች ባለስልጣን (Sidama Roads Authority)


ለመጀመሪያ ዙር የወጣ የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

የግዥ መለያ ቁጥር:-ሲ/መ/ባ/007/2019

ቮልቮ ሎቤድ መኪና የሚውል መለዋወጫ ዕቃ ግዥ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

የሲዳማ መንገዶች ባለስልጣን ለ2019 በጀት ዓመት የተለያዩ መንገድ ለሚያስራቸው ማሽነሪዎች፤ከባድ መኪናዎች የሚውል ቮልቮ ሎቤድ መለዋወጫ ዕቃዎች ግዥ መስፈርቱን ከሚያሟሉ አቅራቢዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ተ/ቁ Description TRUCK Model CHassis Marketing type Quantity
1 Gear Box Assy Volvo FH400 A715146 FH1364T 01

በዚሁ መሠረት:-

  1. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የዘመኑን ግብር የተከፈለበትን ከሚፈለገው አገልግሎት ጋር የተዛመደ የታደሰ የንግድ ሥራ ፍቃድ ወይም የአገልግሎት የሥራ ፍቃድ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ሰርተፍኬት እና የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ታክስ ክሊራንስ እንዲሁም የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ስለመመዝገባቸውን የሚያሳይ ሰርተፍኬት ፤የማጭበርበር ዲርጊት ላለመፈጸም ቃል መግቢያ ደብደቤ በማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  2. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 (አስር) ተከታታይ ቀናት ከባለሥልጣኑ መ/ቤት ግዥ የፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር -5 ቀርበው መግዛት ይችላሉ።
  3. ተጫራቾች ማቅረብ ያለባቸው ኦርጅናል እቃ ከቮልቫ ካንፓን ከዋናው አምራች ማቅረብ አለባቸው ።
  4. ተጫራቾች የጠቅላላ ዋጋ 100,000(አንድ መቶ ሽህ ብር ብቻ) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ ከተረጋገጠ CPO ወይምBid bond በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ከጨረታ ሰነዶች ጋር በማያያዝ ማቅረብ ይኖሪባቸዋል ከዚህ ውጭ በኢንሹራንስ ወይም በሌላ መልክ የሚቀርብ የጨረታ ማስከበሪያ ተቀባይነት የለውም።
  5. ተጫራቾች በጨረታው ደንብና መመሪያ መሠረት ጨረታቸውን ማቅረብ አለባቸው።ከጨረታው ደንብና መመሪያ ውጭ የሚቀርብ ማንኛውም ጨረታ ተቀባይነት የለውም ።
  6. የጨረታ ሰነዱ በተጫራቾች መመርያ መሠረት ተሞልቶ ጨረታ ማስከበርያ /Bid Security/፣ፋይናሻል አንድ ዋና (ኦርጅናል) እና ሁለት ኮፒዎችን እንድሁም ቴክኒካል አንድ ዋና (ኦርጅናል) እና ሁለት ኮፒ ሰነዶችን በተለያየ ፖስታ በሰም በማሸግ ለየብቻቸው ታሽጎ በአንድ እናት ፖስታ ውስጥ ተካተውና በሁሉም ዶክመንት ላይ ስምና አድራሻ በመጻፍ ህጋዊ የሆነ ማህተም በመምታት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከጧቱ 3:00 እስከ 6:00 ሰዓት በሲዳማ መንገዶች ባለሥልጣን በግዥ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ክፍል ለዚሁ አገልግሎት በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። የጨረታ ማስከበሪያው ከቴክኒካል ሠነድ ጋር አብሮ መታሸግ አለበት። ከላይ የተጠቀሰው ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የእረፍት ወይም የህዝብ በዓል ቀን ሆኖ ከዋለ በቀጣይ በሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓትና ቦታ የሚከፈት ይሆናል።
  7. በጨረታ ሰነድ ላይ የተጠቀሱትን የጨረታ መመሪያ እና ህጎች አለማክበር በመጫረቻ ሰነዶቻቸው በሁሉም ገጽ ላይ ማህተምና ፊርማ ያለማድረግ እና ያልተፈረመበት ስረዝ ድልዝ ያለበት የመጫረቻ ሰነድ ተቀባይነት የለውም።
  8. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከላይ የጨረታ መከፈቻ ተብሎ በተጠቀሰው ቀንና ቦታ ከቀኑ 6:00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ ከቀኑ 8:30 ሰዓት ላይ በባለስልጣኑ መ/ቤት አደራሽ ይከፈታል።
  9. ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

• ስልክ ቁጥር:- 0462-128-446

ሲዳማ መንገዶች ባለሥልጣን
ሀዋሳ

✨ messages.ai_summary
Sidama Roads Authority seeks suppliers of an original gear box assembly for its Volvo FH400 lowbed truck, sourced from the original manufacturer. Open bid.
Save Tender