Tender Detail

Tender Details

  • Company የሲዳማ መንገዶች ባለስልጣን (Sidama Roads Authority)
  • Address ሀዋሳ ከተማ ፡ ሲዳማ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0462128588
  • Website
  • Deadline03 Dec 2026, 12:00 PM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • CountryEthiopia
  • Bid Document Priceብር 500.00 (የማይመለስ)
  • Bid Securityሎት-1 ብር 150,000.00፤ ሎት-2 ብር 1,000,000.00 (Bank Guarantee ወይም CPO)
  • opening dateበዚሁ ቀን ከቀኑ 8:30 ሰዓት፣ በባለስልጣኑ መ/ቤት አደራሽ
  • Sector Building Construction

የሲዳማ መንገዶች ባለሥልጣን የአጥር ግንባታ እና የይርጋለም ማጋራ ዲስትሪክት ግንባታ ሥራ

የሲዳማ መንገዶች ባለስልጣን (Sidama Roads Authority)


ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የግዥ መለያ ቁጥር:- ሲ/መ/ባ/004/2019

የሲዳማ መንገዶች ባለስልጣን 2019 በጀት ዓመት በይርጋለም ከተማ አስተዳደር ማጋራ ዲስትሪክት ሊያሰራ ያቀደው

  1. ሎት-1 የአጥር ግንባታ ሥራ
  2. ሎት-2 የይርጋዓለም ማጋራ ዲስትሪክት ግንባታ ሥራ ህጋዊ ተጫራቾችን በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል ::

በዚሁመሠረት:-

  1. ደረጃቸው GC-5/BC-5 እና ከዚሁ በላይ የሆኑ ሥራ ተቋራጮች 2018ዓ/ም ፍቃዳቸውን ያሳደሱና የዘመኑ ግብር የከፈሉ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፤ ፤የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሠርተፊኬት(VAT)፣ የግብር ከፋይ ሰርተፊኬት(TIN) ማቅረብ የሚችሉ ከኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን እና ከሰዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ኮንስትራክሽን ባለስልጣን የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ሰርቴፍኬት ማቅረብ የሚችሉ እና በጨረታ መወዳደር የሚያስችል የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ታክስ ክሊራንስ እንዲሁም ከመንግሥት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ መመዝገባቸውን የሚያሳይ ሰርተፊኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  2. አስፈላግውን የግንባታ ማቴሪያሎች፤የሥራ ማሳሪያዎች እና ሌሎች ሀብቶችን በግላቸው አቅርበው ግንባታውን መስራትና ማጠናቀቅ የሚችሉ።
  3. በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ውስጥ ፕሮጀክቶችን ሠርቶ ለማስረከብ ከአሠሪ እና ከሚመለከታቸው መሥሪያ ቤቶች ጋር ህጋዊ ውል ገብተው በስራ ወቅትከአሠሪ መስሪያ ቤት ወይም ከአማካሪ መስሪያ ቤትማንኛውምዓይነት የሥራ አፈጻፀም ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷው ወደ ሥራ ገብተው ያስተካከሉ ሥራ ተቋራጮች የጨረታ ሰነድ መግዛት ሆነ መወዳደር አይችልም ::
  4. የስራ ተቋራጮች ለወድድር ያቀረቡትን ብቃት (ቴክኒክ) መወዳደሪያ ሰነዶች ዋና (ኦርጅናል)ሲጠየቁ አቅርበው ማመሳከር አለባቸው፤ይህ ተጣርቶ ኮፒው ከዋናው ጋር ተመሳክሮ ትክክለኛ ካልሆነ ተቋራጩ ከውድድር ውጭ ይሆናል።
  5. የጨረታ ማስከበሪያ (bid security) ብር ለሎት-1 150,000.00(አንድ መቶ ሃምሳ ሽህ ብር ብቻ )እና ለሎት-2 1,000,000.00(አንድ ሚሊዮን ብር)በባንክ በተረጋገጠ ዋስትና/Bank Gauantee/ወይም የክፍያ ማዘዣ (CPO) ከመጫረቻ ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል ከባንክ የሚቀርበው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (Bid Bond) ለ120 ቀናት ፀንቶ የሚቆይ መሆን ይኖርበታል። ።ከዚህ ውጭ በኢንሹራንስ ወይም በሌላ መልኩ የሚቀርብ የጨረታ ማስከበሪያ ተቀባይነት የለውም ።
  6. አንድ ተቋራጭ ከአንድ ሎት በላይ መግዛት ሆነ መወዳደር አይችልም።
  7. የሥራ ተቋራጭች በተጫራቾች መመሪያ መሠረትህጋዊ ፈቃዳቸውንና ተ.እ.ታ(Vat) የተመዘገቡበትን ሰርቴፍኬትና ታክስ ክሊራንስ በማቅረብ የጨረታ ዶክመንቱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ ለ20(ሃያ) ተከታታይ ቀናት የማይመለስ ብር 500.00(አምስት መቶ ብር) በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት መንገዶች ባለስልጣን ፋይናንስ ክፍል በመክፈል ሰነዱን መውሰድ ይችላል ።
  8. የሥራ ተቋራች ከጨረታው መዝጊያ ቀን በፊት የግንባታ ሳይት በራሳቸው ወጪ አይቶ ማረጋገጥ አለባቸው።
  9. የጨረታ ሰነዱ በተጫራቾች መመርያ መሠረት ተሞልቶ ጨረታ ማስከበርያ /Bid Security/፣ፋይናሻል አንድ ዋና (ኦርጅናል) እና ሁለት ኮፒዎችን እንዲሁም ቴክኒካል አንድ ዋና (ኦርጅናል) እና ሁለት ኮፒ ሰነዶች በተለያየ ፖስታ በሰም በማሸግ ለየብቻቸው ታሽጎ በአንድ እናት ፖስታ ውስጥ ተካተውና በሁሉም ዶክመንት ላይ ስምና አድራሻ በመጻፍ ህጋዊ የሆነ ማዕተም በመምታት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ22ኛው ቀን ከጧቱ 3:00 እስከ 6:00 ሰዓት በሲዳማ መንገዶች ባለሥልጣን በግዥ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ክፍል ለዚሁ አገልግሎት በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። የጨረታ ማስከበሪያው ከቴክኒካል ሠነድ ጋር አብሮ መታሸግ አለበት። ሆኖም የተጠቀሰው ቀን የእረፍት ወይም የህዝብ በዓል ቀን ሆኖ ከዋለ በቀጣይ በስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ላይ የሚከፈት ይሆናል።
  10. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከላይ የጨረታ መክፈቻ ተብሎ በተጠቀሰው ቀንና ቦታ ከቀኑ 6:00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ ከቀኑ 8:30 ሰዓት ላይ በባለስልጣኑ መ/ቤት አደራሽ ይከፈታል። የተጫራቾች አለመገኘት የጨረታውን መከፈት አያግደውም ።
  11. አሠሪው መ/ቤት የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።ለበለጠ መረጃ ተጫራቾች የሚከተለውን መረጃ መጠቀም ይችላሉ።

• ስልክ ቁጥር:- 0462-128-446

ሲዳማ መንገዶች ባለሥልጣን
ሀዋሳ

Summary
Sidama Roads Authority invites GC-5/BC-5 and above contractors for two lots at its Magara District in Yirgalem town: fence construction and construction of the Yirgalem Magara District. Open bid.
Save Tender