ለተማሪዎቸ ቀለብ የሚዉል የተለያዩ የምግብ ግብዓት ግዥ
Gambella University
Tender Information
| Title | ለተማሪዎቸ ቀለብ የሚዉል የተለያዩ የምግብ ግብዓት ግዥ |
| Description | LOT 001 ለተማሪዎቸ ቀለብ የሚዉል የተለያዩ የምግብ ግብዓት ግዥ |
| Procuring Entity | Gambella University |
| Reference No | GU-NCB-G-0001-2018-BID-Open |
| Procurement Method | Open |
| Submission Deadline | 2025-10-09 15:00:00 |
| Invitation Date | 2025-09-29 00:00:00 |
| Procurement Type | Bidding |
| Award Type | single envelop |
Contact Information
| Physical Address: | Gambella, Room New Campus Admin Building Ground floor to the right side Gambella, Ethiopia, Ethiopia |
| Contact Details: | Tel: +251 917527138 Email: addisuabebe2012@gmail.com |
| Mailing Address: | P.O. Box 126, Postal Code: 0000 |
ProfessionalQualification
- •የተጫራችን ፕሮፌሽናል አቅም የአግባብነት ማረጋገጫ:
በጨረታ መረጃ ሠንጠረዥ ንዑስ አንቀፅ 14.1 መሠረት የተጫራቹ ፕሮፌሽናል አቅም ያለው መሆኑን ለማረጋገጥ የተጠየቀውን የአግባብነት ማረጋገጫ በተሰጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ ማቅረብ ከቻለ፣
(Ref: የ.ተ.መ 37.3(ለ)) - •የፕሮፌሽናልነት (የሙያ ብቃት) ማስረጃ :
በጨረታ ዝርዝር መረጃ ሠንጠረዡ ንዑስ አንቀጽ 4.6 (ለ) (iv) ተጠይቆ ከሆነ ተጫራቹ ተዛማጅነት ያለው የፕሮፌሽናልነት (የሙያ ብቃት) ማስረጃ ማቅረብ ከቻለ፣
(Ref: የ.ተ.መ 37.3(ሀ))
LegalQualification
- •የኤክሳይዝ ታክስ ምዝገባ እና ታክሱ የተከፈለበት ሰርተፍኬት:
የኤክሳይዝ ታክስ የሚከፈልባቸው ምርቶች ሲሆኑ የኤክሳይዝ ታክስ ምዝገባ እና ታክሱ የተከፈለበት ሰርተፍኬት ከታክስ ባለስልጣን ማቅረብ ሲችል
(Ref: የ.ተ.መ 37.2(ሰ)) - •ታክስ የተከፈለበት ሰርቲፊኬት :
በተጫራቾች መመሪያ ንዑስ አንቀጽ 4.6 (ለ) (iii) መሠረት በሚመለከተው አካል የተሰጠ የወቅቱን ግብር የተወጣ ስለመሆኑ የሚያሳይ ታክስ የከፈለበትን ሰርቲፊኬት ከታክስ ባለሥልጣን ማቅረብ ሲችል፣
(Ref: የ.ተ.መ 37.2(ረ)) - • የተጨማሪ ዕሴት ታክስ የምዝገባ ሰርቲፊኬት:
በጨረታ ዝርዝር መረጃ ሠንጠረዥ ንዑስ አንቀጽ 4.6 (ለ) (ii) መሠረት የተጨማሪ ዕሴት ታክስ የሚጠየቅበት ተጫራች ሆኖ ሲገኝ በታክስ ባለሥልጣን የተሰጠ የተጨማሪ ዕሴት ታክስ የምዝገባ ሰርቲፊኬት ማቅረብ ሲችል ፣
(Ref: የ.ተ.መ 37.2(ሠ)) - •የጥቅም ግጭት:
በተጫራቾች መመሪያ ንዑስ አንቀጽ 4.3 መሠረት ተጫራቹ የጥቅም ግጭት የሌለበት መሆኑ ሲታወቅ፣
(Ref: የ.ተ.መ 37.2(ለ)) - •ዜግነት:
በተጫራቾች መመሪያ ንዑስ አንቀጽ 4.2 መሠረት ተጫራቹ ዜግነት ካለው
(Ref: የ.ተ.መ 37.2(ሀ)) - •የጥምረት ወይም የሽርክና ወይም የእሽሙር ማህበር የመረጃ ቅፅ :
በተጫራቾች መመሪያ ንዑስ አንቀጽ 4.1 መሠረት ጨረታው የቀረበው በጥምረት ወይም በሽርክና ወይም በእሽሙር ማህበር ከሆነና ተጫራቹ የጥምረት ወይም የሽርክና ወይም የእሽሙር ማህበሩን የመረጃ ቅፅ፣ ማህበሩ የተቋቋመበትን ስምምነት ወይም ደብዳቤ ማቅረብ ከቻለ፣
(Ref: የ.ተ.መ 37.2(ቀ)) - •የንግድ ፈቃድ :
በተጫራቾች መመሪያ ንዑስ አንቀጽ 4.6 (ለ) (i) መሠረት ተጫራቹ ከሥራው ጋር አግባብነት ያለው የታደሰ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ ሲችል ፣
(Ref: የ.ተ.መ 37.2(ሐ))
FinancialQualification
- •የገንዘብ አይነት :
ተጫራቹ ያቀረበው ዋጋ በጨረታ ዝርዝር መረጃ ሰንጠረዥ እና በተጫራቾች መመሪያ አንቀጽ 13 ላይ በተጠቀሰው የገንዘብ አይነት ከሆነ
(Ref: የ.ተ.መ 37.5 (ሠ)) - •አመታዊ አማካይ የገቢ መጠን :
በክፍል 3 የጨረታ ግምገማ ዘዴና መስፈርቶች በተመለከተው መሰረት የተጫረቹ አመታዊ አማካይ የገቢ መጠን መ/ቤቱ በጨረታ ዝርዝር መረጃ ሰንጠረዥ ከተጠቀሰው አንጻር ሲታይ ካላነሰ
(Ref: የ.ተ.መ 37.5 (ሐ)) - •የፋይናንስ አቅሙን የሚያሳዩ ሌሎች ማረጋገጫ ሰነዶች :
በጨረታ ዝርዝር መረጃ ሠንጠረዥ ንዑስ አንቀጽ 15.2 (ለ) መሠረት ተጫራቹ የፋይናንስ አቅሙን የሚያሳዩ ሌሎች ማረጋገጫ ሰነዶች ሲያቀርብ
(Ref: የ.ተ.መ 37.5 (ለ)) - • በኦዲተር የተረጋገጠ የፋይናንስ ማረጋገጫ :
በጨረታ ዝርዝር መረጃ ሠንጠረዥ ንዑስ አንቀጽ 15.2 (ሀ) እና በክፍል 3 የግምገማ ዘዴና መስፈርቶች በተመለከተው መሠረት ተጫራቹ በተመሰከረለት ኦዲተር የተረጋገጠ የፋይናንስ ማረጋገጫ ሲያቀርብ
(Ref: የ.ተ.መ 37.5 (ሀ)) - •የቀረበ የጨረታ ዋጋ :
ተጫራቹ ለዕቃዎቹና ተያያዥ አገልግሎቶቹ ያቀረበው የጨረታ ዋጋ በጨረታ ዝርዝር መረጃ ሠንጠረዥ አንቀጽ 12 በተገለጸው መሠረት ከሆነ፣
(Ref: የ.ተ.መ 37.5 (መ))
TechnicalQualification
- • የማስረከቢያና ማጠናቀቂያ ጊዜ መግለጫ :
ተጫራቹ በክፍል 6 በተመለከተው መሠረት ቀን ያለበት የማስረከቢያና ማጠናቀቂያ ጊዜ መግለጫ ፡፡
(Ref: የ.ተ.መ 37.4 (ሠ)) - •ከአምራቹ የተሰጠ የአቅራቢነት የውክልና ደብዳቤ :
በአንቀጽ 5.6 መሠረት እንደአስፈላጊነቱ ተጫራቹ ከአምራቹ የተሰጠ የአቅራቢነት የውክልና ደብዳቤ ሲቀርብ
(Ref: የ.ተ.መ 37.4(መ)(iii)) - •የዕቃዉ ሥሪት ሀገር መነሻ:
ተጫራቹ የጨረታ ማስረከቢያ ቅፅ በሚፈቅደው መሠረት የዕቃዎቹንና ተያያዥ አገልግሎቶቹን መነሻ ሀገር ከየት እንደሆነ መግለፅ አለበት::
(Ref: የ.ተ.መ 37.4(ሀ) ) - •ዋስትና:
በአጠቃላይ የውል ሁኔታዎች አንቀጽ 23 መሠረት ድርጅቱ ዋስትና ሲቀርብ
(Ref: የ.ተ.መ 37.4(መ)(ii)) - •የቴክኒክ መግለጫ ፅሑፍ :
በተጫራቾች መመሪያ አንቀጽ 17 መሠረት ተጫራቹ የቴክኒክ መግለጫ ፅሑፍ ካቀረበ፣
(Ref: የ.ተ.መ 37.4(መ)(i)) - •ዋና ዋና የውል ስምምነቶች አፈጻጸም መረጃ:
ተጫራቹ የጨረታ ዝርዝር መረጃ ሠንጠረዥ በሚጠይቀው መሠረት ከዚህ በፊት በአጥጋቢ ሁኔታ ያከናወናቸው ዋና ዋና የውል ስምምነቶች አፈጻጸም መረጃ በቁጥርና በጊዜ ለይቶ በተጫራቾች አግባብነት ማረጋገጫ ቅፅ ማቅረብ አለበት፣
(Ref: የ.ተ.መ 37.4(ለ) ) - •የአቅርቦት ውል ስምምነቶች የሚያረጋግጥ ማስረጃ በጊዜና በበጀት :
ተጫራቹ በጨረታ ዝርዝር መረጃ ሠንጠረዥ ንዑስ አንቀጽ 16.3 መሠረት ከዚህ በፊት ከሰራላቸው አካላት የአቅርቦት ውል ስምምነቶችን በአጥጋቢ ሁኔታ ማከናወኑን የሚያረጋግጥ ማስረጃ በጊዜና በበጀት ለይቶ ማቅረብ አለበት
(Ref: የ.ተ.መ 37.4(ሐ) )
Bid Security
Amount: 500000 ETB
SME Bid Security Form: Letter_from_Small_and_Micro_Enterprise
Local Bidders Form: Bank_Guarantee
Terms and Conditions
ዋጋ ሲሞሉ በዝርዝር መስፈርቱ እና መለኪያውን በጥንቃቄ በመመልከት ይሙሉ፡፡
ንብረቱን ጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ግቢ መጋዘን ድረስ አጓጉዘው የሚያስረክቡ መሆኑ ይታወቅ፡፡
ህጋዊነቱን ለማረጋገጥ ይረዳን ዘንድ ለጨረታው የተጠየቀውን የጨረታ ማስከበሪያ በሲስተሙ ላይ መለጠፍዎ እንዳለ ሆኖ ከጨረታው መክፈቻ ሰዓት በፊት ኦርጅናሉን ዩንቨርሲቲው ግዥ ክፍል ቢሮ ድረስ ተጫራቹ ማቅረብ አለበት፡፡ ነገር ግን በአካል ካላቀረበ በጨረታው ለመሳተፍ ያስገባው የጨረታ ሰነድ የማይከፈት መሆኑ ግልጽ ይሁን፡፡
ተጫራቹ የተሰማሩበት የንግድ መስክ ተዛማጅ ካልሆነ ከውድድር ውጪ ያስደርጋል፡፡
ማንኛውም ተጫራች ለውድድር የሚያቀርባቸው ሰነዶች ህጋዊነታቸው የተረጋገጠ መሆን ይኖርበታል፡፡
ተጫራቾች በአነስተኛና ጥቃቅን የተደራጁ ማህበራት ከሆኑ ካደራጃቸው አካል የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚሆን በሲስተሙ ላይ የተገለጸውን የገንዘብ መጠን ተጠቅሶ ዋስትናውን የሚወስድ መሆኑን የሚገልጽ በአደራጃቸው መ/ቤት የበላይ ኃላፊ ብቻ የተፈረመ ደብዳቤ ማቅረብ አለባቸው፡፡
-ማንኛውም ተጫራች ጨረታው በተዘጋ 30 /ሰላሳ/ ደቂቃ ውስጥ የመክፈቻ ሚስጥር ቁጥር በሲስተሙ ብቻ መላክ የሚኖርበት ሲሆን ቁልፉን ያላከ ተጫራች የጨረታ ሰነዱ ሳይከፈት ቀርቶ የላኩትን ብቻ የምናስተናግድ እና ግምገማው የሚከናወን ይሆናል፡፡
ዩኒቨርሲቲው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
