የግንባታ ዕቃዎች
Addis Ababa Road Authority
Tender Information
| Title | የግንባታ ዕቃዎች |
| Description | የግንባታ ዕቃዎች |
| Procuring Entity | Addis Ababa Road Authority |
| Reference No | AACRA-NCB-G-0016-2018-BID-Open |
| Procurement Method | Open |
| Submission Deadline | 2025-12-04 10:00:00 |
| Invitation Date | 2025-11-21 00:00:00 |
| Procurement Type | Bidding |
| Award Type | two envelop |
Contact Information
| Physical Address: | pushkin, Room 1 Adiss abeba, Ethiopia |
| Contact Details: | Tel: +251 113722815 Email: SoSiown4@gmail.com |
| Mailing Address: | P.O. Box 9206, Postal Code: 1000 |
TechnicalQualification
- •ናሙና ግምገማን በተመለከተ: በተጫራቾች የቀረበዉ ናሙና ባለስልጣን መ/ቤቱ በሚያዋቅራቸዉ የቴክኒክ ኮሚቴ የቴክኒክ ግምገማ ይካሄዳል፡፡የቴክኒክ ግምገማዉን ያለፉ ተጫራቾች የናሙና ግምገማዉን ላለፉባቸዉ እቃዎች ብቻ ፋይናንሻል ግምገማ ይካሄዳል፡፡ናሙና ያላቀረበ ተጫራች ከዉድድር ዉጭ ይሆናል (Ref: 18.1)
- •ናሙና በተመለከተ: ተጫራቾች በዚህ ጨረታ ሰነድ ክፍል 6 የፍላጎቶች መግለጫ ውስጥ በዝርዝር የቀረቡትን ዕቃዎች በዝርዝር መግለጫው መሰረት ለሚወዳደሩበት እቃ ናሙና ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡የሚቀርቡት የናሙና መጠን መለኪያ በጨረታ ሰነዱ በተቀመጠው መሰረት ለእያንዳንዱ በሚወዳደሩበት ዕቃዎች መለኪያ መሰረት አንድ አንድ ((መለኪያዉ በኪ.ግ ከሆነ አንድ ኪ.ግ ፣በቁጥር ከሆነ አንድ፣ በፓኬት ከሆነ አንድ ፓኬት) ) ናሙና ጨረታው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ባሉት የስራ ቀናት ጨረታዉ ከመዘጋቱ አንድ ቀን በፊት መካኒሳ ጀርመን አደባባይ አካባቢ በሚገኘዉ የባለስልጣን መ/ቤቱ ግምጃ ቤት ማቅረብ አለባቸው፡፡ተጫራቾች ናሙና ያስገቡበትን ጊዜዊ መረካከበያ ቅፅ ከመጫረቻ ሰነዳችሁ ጋር ማያያዝ ይኖርባችኋል፡፡ (Ref: 18.1)
LegalQualification
- •ዜግነት:
ተጫራቹ ከዜግነት አወሳሰን ጋር በተያያዘ በተጫራቾች መመሪያ ንዑስ አንቀጽ 4.2 ላይ የተገለፀውን ካላሟላ፣
(Ref: 4.2) - •የጋራ ማህበሩን የመረጃ ቅፅ፣ :
በተጫራቾች መመሪያ ንዑስ አንቀጽ 4.1 መሠረት ጨረታው የቀረበው ከጋራ ማህበር ከሆነና ተጫራቹ የጋራ ማህበሩን የመረጃ ቅፅ፣ ማህበሩ የተቋቋመበትን ስምምነት ማቅረብ ካልቻለ፣
(Ref: 4.1 ) - •በመንግሥት ግዥ እንዳይሳተፍ በመንግሥት ግዥና ንብረት ባለስልጣን የታገደ :
በተጫራቾች መመሪያ ንዑስ አንቀጽ 4.4 መሠረት ከዚህ በፊት ከነበሩ የኮንትራት ግዴታዎች ጋር በተያያዘ ምክንያት በመንግሥት ግዥ እንዳይሳተፍ በመንግሥት ግዥና ንብረት ባለስልጣን የታገደ ተጫራች ከሆነ፣
(Ref: 4.4) - •የንግድ ምዝገባ ሰርቲፊኬት ወይም የንግድ ፈቃድ:
በተጫራቾች መመሪያ ንዑስ አንቀጽ 4.6 (ሐ) መሠረት የውጭ ሀገር ተጫራች ሆኖ ከተቋቋመበት ሀገር የንግድ ምዝገባ ሰርቲፊኬት ወይም የንግድ ፈቃድ ማቅረብ ሳይችል ሲቀር፣
(Ref: 4.6 (ሐ)) - •ታክስ የከፈለበትን ሰርቲፊኬት :
በተጫራቾች መመሪያ ንዑስ አንቀጽ 4.6 (ለ) (iii) መሠረት የሀገር ውስጥ ተጫራች ሆኖ ታክስ የከፈለበትን ሰርቲፊኬት ከታክስ ባለሥልጣን ማቅረብ ሳይችል ሲቀር፣
(Ref: 4.6 (ለ) (iii) ) - •የተጨማሪ እሴት የምዝገባ ሰርቲፊኬት :
በጨረታ ዝርዝር መረጃ ሠንጠረዥና በተጫራቾች መመሪያ ንዑስ አንቀጽ 4.6 (ለ) (ii) መሠረት የሀገር ውስጥ ተጫራች ሆኖ በታክስ ባለሥልጣን የተሰጠ የተጨማሪ እሴት ታከለ የምዝገባ ሰርቲፊኬት ማቅረብ ሳይችል ሲቀር፣
(Ref: 4.6 (ለ) (ii)) - •በመንግሥት ግዥና ንብረት ባለስልጣን ድረ-ገፅ ላይ መመዝገብ :
በተጫራቾች መመሪያ ንዑስ አንቀጽ 4.7 መሠረት ተጫራቹ በመንግሥት ግዥና ንብረት ባለስልጣን ድረ-ገፅ ላይ ያልተመዘገበ ሲሆን፣ (የሀገር ውስጥ ተጫራቾች ብቻ ይመለከታል)፣
(Ref: 4.7) - •የታደሰ የንግድ ፈቃድ :
በተጫራቾች መመሪያ ንዑስ አንቀጽ 4.6 (ለ) (i) መሠረት ተጫራቹ ከሥራው ጋር አግባብነት ያለው የታደሰ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ ሳይችል ሲቀር፣
(Ref: 4.6 (ለ) (i) ) - •የጥቅም ግጭት :
በተጫራቾች መመሪያ ንዑስ አንቀጽ 4.3 መሠረት ከተጫራቹ ጋር የጥቅም ግጭት መኖሩ ሲታወቅ፣
(Ref: 4.3)
FinancialQualification
- •የጨረታ ዋጋ ዝርዝር ሠንጠረዥ :
ተጫራቹ ያቀረበው የጨረታ ዋጋ በጨረታ ዝርዝር መረጃ ሠንጠረዥ አንቀጽ 12 መሠረት ካልሆነ፣
(Ref: 37.5 (መ)) - •የመጫረቻ ገንዘብ :
ተጫራቹ ለመጫረት ያቀረበው የመጫረቻ ገንዘብ በጨረታ ዝርዝር መረጃ ሠንጠረዥና በተጫራቾች መመሪያ አንቀጽ 13 ካልሆነ፣
(Ref: 13)
Bid Security
Amount: 200000 ETB
SME Bid Security Form: CPO, Letter_from_Small_and_Micro_Enterprise, Bank_Guarantee
Local Bidders Form: Bank_Guarantee, CPO
Terms and Conditions
ተጫራቾች ናሙና ያስገቡበትን ጊዜዊ መረካከበያ ቅፅ ከመጫረቻ ሰነዳችሁ ጋር ማያያዝ ይኖርባችኋል፡፡
ባለስልጣን መ/ቤቱ ጨረታዉን በሙሉ ወይም በከፊል የመረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ::
