Tender Detail

Tender Details

  • Company Addis Ababa Road Authority
  • Address Pushkin, Addis Ababa, Ethiopia, Phone: +251113713400
  • Website
  • Deadline17 Apr 2026, 11:00 AM
  • magazineEGP
  • CountryEthiopia
  • Official noticeproduction.egp.gov.et
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid Security500000
  • opening date2026-04-17 11:30:00
  • Sector Goods

የተለያዩ አስፋልት ኮንክሪት ሚክሶች (Asphalt Mix) T-1

Addis Ababa Road Authority


Tender Information

Titleየተለያዩ አስፋልት ኮንክሪት ሚክሶች (Asphalt Mix) T-1
Descriptionየግንባታ እቃዎች ግዥ
Procuring EntityAddis Ababa Road Authority
Reference NoAACRA-NCB-G-0112-2018-BID-Open
Procurement MethodOpen
Submission Deadline2026-04-17 11:00:00
Invitation Date2026-04-07 00:00:00
Procurement TypeBidding
Award Typesingle envelop

Contact Information

Physical Address:pushkin, Room 1st
addis ababa, Ethiopia
Contact Details:Tel: +251 113722815
Email: aacra@gmail.com
Mailing Address:P.O. Box 9206, Postal Code: 1000

LegalQualification

  • •የታደሰ የንግድ ፈቃድ :

    ተጫቾች ለ2018 ዓ.ም የታደሰ ንግድ ፍቃድ ማቅረብ አለባቸው

    (Ref: 4.6 (ለ) (i) )
  • •ዜግነት:

    ተጫራቹ ከዜግነት አወሳሰን ጋር በተያያዘ በተጫራቾች መመሪያ ንዑስ አንቀጽ 4.2 ላይ የተገለፀውን ካላሟላ፣ 

    (Ref: 4.2)
  • •የጋራ ማህበሩን የመረጃ ቅፅ፣ :

    በተጫራቾች መመሪያ ንዑስ አንቀጽ 4.1 መሠረት ጨረታው የቀረበው ከጋራ ማህበር ከሆነና ተጫራቹ የጋራ ማህበሩን የመረጃ ቅፅ፣ ማህበሩ የተቋቋመበትን ስምምነት ማቅረብ ካልቻለ፣

     

    (Ref: 4.1 )
  • •በመንግሥት ግዥ እንዳይሳተፍ በመንግሥት ግዥና ንብረት ባለስልጣን የታገደ :

    በተጫራቾች መመሪያ ንዑስ አንቀጽ 4.4 መሠረት ከዚህ በፊት ከነበሩ የኮንትራት ግዴታዎች ጋር በተያያዘ ምክንያት በመንግሥት ግዥ እንዳይሳተፍ በመንግሥት ግዥና ንብረት ባለስልጣን የታገደ ተጫራች ከሆነ፣

    (Ref: 4.4)
  • •ታክስ የከፈለበትን ሰርቲፊኬት :

    በተጫራቾች መመሪያ ንዑስ አንቀጽ 4.6 (ለ) (iii) መሠረት የሀገር ውስጥ ተጫራች ሆኖ ታክስ የከፈለበትን ሰርቲፊኬት ከታክስ ባለሥልጣን ማቅረብ ሳይችል ሲቀር፣

    (Ref: 4.6 (ለ) (iii) )
  • •የተጨማሪ እሴት የምዝገባ ሰርቲፊኬት :

    በጨረታ ዝርዝር መረጃ ሠንጠረዥና በተጫራቾች መመሪያ ንዑስ አንቀጽ 4.6 (ለ) (ii) መሠረት የሀገር ውስጥ ተጫራች ሆኖ በታክስ ባለሥልጣን የተሰጠ የተጨማሪ እሴት ታከለ የምዝገባ ሰርቲፊኬት ማቅረብ ሳይችል ሲቀር፣ 

    (Ref: 4.6 (ለ) (ii))
  • •የጥቅም ግጭት :

    በተጫራቾች መመሪያ ንዑስ አንቀጽ 4.3 መሠረት ከተጫራቹ ጋር የጥቅም ግጭት መኖሩ ሲታወቅ፣

    (Ref: 4.3)
  • •የንግድ ምዝገባ ሰርቲፊኬት :

    በተጫራቾች መመሪያ ንዑስ አንቀጽ 4.6 (ሐ) መሠረት የውጭ ሀገር ተጫራች ሆኖ ከተቋቋመበት ሀገር የንግድ ምዝገባ ሰርቲፊኬት ማቅረብ ሳይችል ሲቀር፣

    (Ref: 4.6 (ሐ))
  • •የግብር መለያ ቁጥር:

    ተጫራቾች የግብር መክፈያ መለያ ቁጥር (TIN) ማቅረብ አለባቸው

    (Ref: 4.8)
  • •ጨረታ መስከበሪያ:

    ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ ወይም ሲፒኦ ስካን አድርገው ማስገባት አለባቸው፡፡ዋናውን ጨረታው ከሚከፈትበት ቀን ቀደም ብለው 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 105 ማቅረብ አለባቸው

    (Ref: 4.8)

TechnicalQualification

  • •የባለቤትነት ማረገጋጫ ሰነድ:

    ተጫራቹ የራሱ የሆነ የአስፋልት ማምረቻ ፕላንት ክሬሸርና የማምረቻ ኳሪ ሊኖረዉ ይገባል የባለቤትነት ማረገጋጫ ሰነድ ሊብሬ በውልና መስረጃ የተመዘገበ ውክልና ወይም ለዚህ ጨረታ የአቅርቦት ጊዜ የሚሸፍን የኪራይ ውል ለውል ዘመኑ የሰነድ ማረጋጋጫ ማቅረብ አለበት ማረጋገጫ ያላቀረበ ተጫራች ከውድድር ውጭ ይደረጋል፡፡

    (Ref: 3.9)
  • •አቅርቦት መጀመሪያ ጊዜ:

    ተጫራቹ አሸናፊ ሆኖ ውል ከፈረመ በኋላ ባሉት ተከታታይ በ5 /አምስት/ቀናት ውስጥ አቅርቦት ለመጀመር እንደሚችል የፅሁፍ ማረጋገጫ ማቅረብ ይኖርበታል በፅሁፍ ማረጋገጫ ያላቀረበ ተጫራች ከጨረታ ውድድር ውጭ ይደረጋል፡፡

    (Ref: 3.10)
  • •የማምረት አቅም:

    ተጫራቾች በጨረታው የተጠየቁትን ምርቶች በድምሩ በቀን 1000 ቶን  እና ከዛ በላይ የማምረት አቅም እንዳለው ማረጋገጫ ማቅረብ ያለባቸው ሲሆን ማሽኑ ካልብሬት የተደረገበት ህጋዊ ሰነድ ማቅረብ አለባቸው እነዚህን ሰነዶች ማቅረብ ያልቻለ ተጫራች ከውድድር ውጭ ይደረጋል፡፡የማምረት አቅም ሊኖራቸው ይገባል 

    (Ref: 3.8)
  • •ፍላጎት መግለጫ:

    የጨረታው አሸናፊ የሚያቀርበው ምርት በጨረታ ሰነዱ ክፍል 6 በተገለፀው የቴክኒክ ዝርዝር ፍላጎት መግለጫ መሰረት የሚያሟላ መሆኑን ይኖርበታል፡፡ የሚያቀርበው ምርት ጥራት በተመለከተ በጨረታ ሰነዱ ክፍል 6 የተቀመጠውን የጥራት መግለጫ (specification) መሰረት መሆኑን በፅሁፍ ያላረጋገጠ ተጫራች ከጨረታ ውድድር ውጭ ይደረጋል፡፡

    (Ref: 3.4)
  • •የክብደት ልኬት:

    ተጫራቾች በእያንዳንዱ ጭነት ለሚያቀርበው ምርቱን ክብደት መጠኑ መለካት ያለበት ሲሆን በማምረቻ ቦታው የምድር ሚዛን ወይም Control Room print out ያለው መሆኑን በፅሁፍ ማረጋገጫ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡ የምድር ሚዛን ወይም Control Room print out የሌለው ወይም የፅሁፍ ማረጋገጫ ያላቀረበ ተጫራች በቴክኒክ ግምገማ ወቅት ከጨረታ ውድድር ውጭ ይደረጋል፡፡

    (Ref: 3.13)
  • •ፕላንት ብልሽት ቢያጋጥም:

    አሸናፊ ተጫራቾች ውል ከገባ በኋላ በፕላንቱ ላይ በብልሽት በጥገና በመሳሰሉት ምክንያቶች ግዥ ፈፃሚው አቅርቦት እንዳይስተጓጎል ማድረግ ግዴታ ይኖርበታል፡፡ 

    (Ref: 3.13)
  • •የጨረታ አሸናፊ :

    በቴክኒክ ግምገማ መስፈርቱን ያሟሉ ተጫራቾች ብቻ ያቀረቡት ዋጋ ለእያንዳንዱ ምርት በአንድ ቶን /በነጠላ ዋጋ/የሚወዳደሩ ሲሆን ለ1ቶን የቀረበው ዝቅተና ነጠላ ዋጋ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረቱ ቅናሾችን ጨምሮ ተጨማሪ እሴት ታክስና የትራንስፖርት ዋጋ ጨምሮ የጨረታው አሸናፊ ይሆናል

    (Ref: 3.16)

PerformanceQualification

  • •መልካም ስራ አፈጻጸም:

    ማንኛውም ተጫራች ወይም አቅራቢ ላለፉት 2 ዓመታት ውስጥ ከባለስልጣን መ/ቤቱ ጋር በአግባቡ ያልፈጸመው ውል ካው ወይም በእያንዳንዱ በዚህ ጨረታ ባቀረበው ምርት ዓይነት ውል ኖሮት ደካማ የውል አፈጻጸም ያለው በግልግል ወይል የአስተዳደራዊ ውሳኔ የተሰጠበት ተጫራች በዚህ ጨረታ ተቀባይነት አይኖረውም 

    (Ref: 3.7)
  • •የውል አፈጻጸም:

    ማንኛውም ተጫራች ከባለስልጣን መ/ቤቱ ጋር ውል ኖሮት የአቅርቦት አፈጻጸም ከ80% በታች ከሆነ በዚህ ጨረታ መሳተፍ አይችልም

    (Ref: 3)

FinancialQualification

  • •የፋይናንስ አቅም :

    በጨረታ ዝርዝር መረጃ ሰንጠረዥ ንዑስ አንቀጽ 15.2 (ለ) መሰረት ተጫራቾች ይህን ውል በተገቢው መንግድ ለማከናወን በቂ የፋይናንስ አቅም ያለው መሆኑን በሚያሳይ መልኩ የጨረታ ዝርዝር መረጃ ሰንጠረዥ በሚያዘው መሰረት በክፍል 4 የተመለከተውን የተቻራቾች የሙያ ብቃት ማረጋገቻ ሞልተው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ወይም ይህን ውል ለማከናወን የሚያስችል የፋይናንስ ድጋፍ የብድር ስምምነት ከታወቀ ባንክ ቢያንስ 50 ሚሊዮን ብር በማቅረብ ማረጋገጥ ይኖርባቸዋል ወይም የፋይናንስ አቅማቸውን የሚሳይ ከታወቀ ባንክ የተረጋገጠ የሂሳብ መግለቻ ማቅረብ ይኖርባቸዋል

    (Ref: 3.6)
  • •የኦዲት ሪፖርት:

    ተጫራቾች ያልከሰረ መሆኑን ይህን ውል በተገቢው መንገድ ለማከናወን በቂ የሆነ የፋይናንስ አቅም ያለው መሆኑን በሚያሳይ በገለልተኛ ኦዲተር የተረጋገጠ ያለፉት 2 ዓመታት የኦዲት ሪፖርት ማቅረብ አለባቸው 

    (Ref: 3.3)

Bid Security

Amount: 500000 ETB

SME Bid Security Form: Bank_Guarantee, CPO

Local Bidders Form: Bank_Guarantee, CPO

Terms and Conditions

ተጫራቾች ኪ ሼር ማድረግ አለባቸው
ባለስልጣን መ/ቤቱ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው
Save Tender