Tender Detail

Tender Details


የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ሰፈደራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን ፕሮጀክት አገልግሎት የሚውል


ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥርDCE/SF/119/2026

የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ሰፈደራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን ፕሮጀክት አገልግሎት የሚውል

በታች በሠንጠረዥ በዝርዝር የተጠቀሰውን Supply & fix IP TV and digital Signage ሥራ ግዥ ለመፈፀም ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ተ/ቁ የዕቃውን አይነት የፕሮጀክት ስም የጨረታ ቁጥር የጨረታ መዝጊያ ቀን እና ሰዓት የጨረታ መከፈቻ ቀን እና ሰዓት የጨረታ ማስከበሪያ
  Supply & fix IP TV and digital Signage ፈደራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን DCE/5/89/2026 መስከረም 13/2019 ዓም 4:00 ሰዓት መስከረም 13/2019 ዓም 4:15 ሰዓት 200,000.00
  1. ተጫራቾች በዘርፍ የተሰማሩ መሆኑን የሚገልጽ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉበት ማስረጃ፣ ለተጨማሪ አሴት ታክስ የተመዘገቡበትን ግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ በጨረታ ለመሳተፍ የሚሰጥ የታደሰ የምስክር ወረቀት (ታክስ ክሊራንስ) እና የአገር ውስጥ ተጫራቾች በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ ኮፒ ወዘተ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
  2. ተጫራቾች ከላይ በሰንጠረዡ በተገለጸው መሠረት የጨረታ ማስከበሪያ ቦንድ (Bid Bond) 120 ቀን ፀንቶ የሚቆይ ለያንዳንዱ ጨረታ ቁጥር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ የጨረታ ማስከበሪያው እንደ ተጫራቹ ምርጫ በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ በባንክ ዋስትና (Unconditional Bank Guarantee) ወይም በባንክ የተሰጠ የተረጋገጠ ቼክ (CPO) መቅረብ ይኖርባቸዋል፡ የመድን ድርጅቶች ዋስትና ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
  3. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ በጨረታ ሰነድ በተያያዘው ዝርዝር መሠረት መሆን ይኖርበታል፡፡
  4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ዘወትር በሥራ ሰዓት የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ዋና መ/ቤት አዲሱ ቢሮ ቃሊቲ ቶታል ማደያ ዝቅ ብሎ የቀድሞ መኮድ ግቢ ውስጥ
  5. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የጨረታ ቴክኒካል ሰነድ እና ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎፕ ከላይ በሰንጠረዡ በተገለጸው ቀንና ሰዓት በኢንተርፕራይዙ የግዥና አቅርቦት አስተዳደር መምሪያ ቢሮ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  6. ጨረታው በሰንጠረዡ በተገለጸው መሠረት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
  7. ኢንተርፕራይዙ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ የቀጥታ ስልክ ቁጥር 0911171751/0913297297

E-mail አድራሻ Info@dce-et.com

የድህረ ገፅ አድራሻ www.dce-et.com

ቃሊቲ ቶታል ማደያ ዝቅ ብሎ የቀድሞ መኮድ ግቢ

የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ

✨ messages.ai_summary
Defense Construction Enterprise seeks bids to supply and fix IP TV and digital signage for the Federal Prison Commission project. Bidders must provide a renewed business license, tax clearance, VAT registration, and supplier registration.
Save Tender