Tender Detail

Tender Details

  • Company የደ/ብርሃን እንጨት ማቀነባበሪያ ኃ/የተ/የግል ማህበር
  • Address , Phone: 011 637 58 03
  • Website
  • Deadline26 Sep 2026, 10:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Priceብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/
  • opening date4፡30 ሰዓት
  • Categories Cargo Vehicle , Transportation Service And Cargo

የደ/ብርሀን እንጨት ማቀነባበሪያ ኃ/የተ/የግል ማህበር በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመከራየት ይፈልጋል፡፡


የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

የደ/ብርሀን እንጨት ማቀነባበሪያ ኃ/የተ/የግል ማህበር ለሚያመርተው ቤኒር እና ፕላይ ውድ ጣውላ ግብዓት የሚሆን የባህርዛፍ ግንድ ጫካው ከሚገኝበት ከደ/ብርሃን ወደ ደሴ በሚወስደው መንገድ ከሚገኘው ሎት 1፡- ጉዶበረት ቀበሌ ልዩ ስሙ ጀርባ ምድር ደን ሳይት በግምት 150 ቢያጆ እና ሎት 2፡- አባሞቴ ቀበሌ ልዩ ስሙ ቡራ ደን ሳይት በግምት 150 ቢያጆ የተቆረጠ ግንድ የሚያመላልሱ ገልባጭ መኪኖችን በዘርፉ የተሰማሩ ባለንብረቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ አሸናፊ ከሆነው ባለንብረት ጋር የኮንትራት ውል በመግባት ግንዱ ተጭኖ እስከሚያልቅ ድረስ ለመከራየት ይፈልጋል፡፡ በዚህ መሰረት፦

  1. በዘርፉ የተሰማራና የንግድ ስራ ፈቃዱን ያሳደሰ
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን ነምበር/ ያላቸው
  3. የቫት ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፤
  4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትና ሌሎች የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. ተጫራቾች ለሁለቱም የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሎት 1-20,000.00 /ሃያ ሺህ ብር/ እና ለሎት 2-20,000.00 /ሃያ ሺህ ብር/ ለሁለቱም ሎቶች ለየብቻ በባንክ በተረጋገጠ የከፍያ ትእዛዝ /CPO/ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  6. ተጫራቾች በሚያቀርቡት ሰነድ ላይ ስማቸውን፣ ፈርማቸውንና አድራሻቸውን ማስፈርና የድርጅቱን ማህተም ማድረግ አለባቸው፡፡
  7. በመጫረቻ ሰነዱ ላይ ምንም አይነት ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም፤ ካለም አንድ ሰረዝ በማድረግ ፊርማቸውን ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል፤
  8. ድርጅቱ ከፍያ የሚፈፅመው በቢያጆ ስለሆነ ለመኪናው የሚያስፈልገውን ወጭ የነዳጅ እና ሌሎች ሁሉንም ወጭዎች የሚሸፍነው ባለመኪናው ይሆናል፡፡
  9. ተጫራቾች አሪጅናል የጨረታ ሰነድ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በካምፓኒው የፋይናንስ ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 16 ቀናት የሚቆይ ስለሆነ ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ የጨረታውን ሰነድ ገቢ ማድረግ ይችላሉ፡፡
  10. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ላይ ታሽጎ 4፡30 ሰዓት ላይ በካምፓኒው የፋይናንስ ቢሮ ውስጥ በይፋ ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ባይገኙም ከመከፈት አይታግድም፡፡
  11. የመከፈቻ ቀኑ የህዝብ በዓል ወይም እሁድ ቀን ከዋለ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
  12. አሸናፊ ሆኖ የተመረጠው ተጫራች የውል ማስከበሪያ የሚሆን ገንዘብ በሲፒአ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ብር ለሎት 1- 100,000.00 /አንድ መቶ ሺህ ብር/ እና ለሎት 2፡- 100000.00/አንድ መቶ ሺህ ብር ለሁለቱም ሎቶች ለየብቻ ማስያዝ አለበት፣ ሆኖም ያሸነፈው ተጫራች አንዱን ሎት ብቻ ከሆነ የሚያስይዘውም የውል ማስከበሪያ የአንዱን ብቻ ይሆናል፡፡
  13. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ ከካምፓኒው ፋይናንስ ቢሮ መግዛት ይችላሉ፡፡
  14. መ/ቤቱ የተሸለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0910368437 ደውለው ይጠይቁ

ማህበር የደ/ብርሀን እንጨት ማቀነባበሪያ ኃ/የተ/የግል ማህበር ደብረ ብርሃን

✨ messages.ai_summary
The association seeks to rent debarking vehicles to transport felled logs from two forest sites to Dessie. Bidders must be licensed in the sector, have a renewed business license, TIN, and VAT registration. The contractor covers all fuel and other vehicle costs.
Save Tender