Tender Detail

Tender Details


በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአ/ከ/ከ/ከ በወረዳ 10 ስር የሚገኘው የብርሃን በር ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ከመንግሥት ከተመደበለት መደበኛ እና ውስጥ ገቢ በጀት ለ2019 ዓ.ም አገልግሎት ላይ የሚውሉ የተለያዩ አይነት እቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።


ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 01/2018

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአ/ከ/ከ/ከ በወረዳ 10 ስር የሚገኘው የብርሃን በር ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ከመንግሥት ከተመደበለት መደበኛ እና ውስጥ ገቢ በጀት ለ2019 ዓ.ም አገልግሎት ላይ የሚውሉ የተለያዩ አይነት እቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

ሎት 1 - የደንብ ልብስ (የልብስ ስፌትን ያካትታል) ሎት 2 አላቂ የቢሮ እቃዎች ሎት 3 አላቂ የትምህርት እቃዎች ሎት 4 - ሌሎች አላቂ እቃዎች ሎት 5 ህትመት ሎት 6 የተለያዩ መፅሐፍት ሎት 7 ቋሚ እቃዎች ለመግዛት የሚፈልግ ሲሆን የሚከተሉትን የጨረታ መስፈርት የሚያሟሉ ተጫራቾችን እንዲወዳደሩ ይጋብዛል፡

  • ተጫራቾች የ2017 ዓ.ም የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፤
  • የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) የተሰጠው፤
  • ወቅታዊ የ2017 ዓ.ም የግብር ግዴታቸውን የተወጡና በጨረታው መሳተፍ የሚችሉ መሆኑን የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ።
  • በኢፌዴሪ የመንግሥት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ በአቅራቢነት ሊስት (SUPPLIER LIST) ውስጥ የተመዘገቡ፤
  • በጨረታ መሳተፍ የሚችሉ መሆኑን የሚገልጽ የጨረታ ተሳትፎ ከገቢዎችና ጉምሩክ ጽ/ቤት ቀኑ ያላለፈበት ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 /አስር/ ተከታታይ የሥራ ቀናት የማይመለስ ብር 400.00 /አራት መቶ ብር/ በመከፈል ከብርሃን በር ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ፋይናንስ ክፍል ከጧቱ 2፡30-11፡30 ሰዓት ድረስ መግዛት የሚችሉ መሆኑን እየገለጽን ተጫራቾች በገዙት የጨረታ ሰነድ በእያንዳንዱ ገፅ ላይ ሕጋዊ የድርጅት ማህተምና ፊርማ ማድረግ ይኖርባቸዋል። ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በጨረታ ሰነድ ውስጥ በሚገኘው የእቃዎች ዝርዝር ላይ የእያንዳንዱን ዋጋ በመሙላት በታሸገ ኢንቨሎፕ ሰነዱን አሸገው ዋናውን እና ኮፒውን ለያይተው ጨረታው እስከሚያበቃበት 10ኛው ቀን እስከ 1፡30 ድረስ ማስገባት ይችላሉ፡፡ ጨረታው በ11ኛው የሥራ ቀን ከዋለ ከጧቱ 4፡00 ታሽጎ በዕለቱ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ተጫራቾች ባይገኙም ጨረታውን ከመከፈት አያስተጓጉለውም። የጨረታ መዝጊያና መክፈቻ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሣሣይ ሠዓት ይከፈታል ማንኛም ተጫራች መጫረት የሚችለው በሚመለከተው የንግድ ሥራ ፍቃድ (ሥራ ዘርፍ) ብቻ ነው። ከጥቃቅንና አነስተኛ ተደራጅታችሁ የዋስትና ደብዳቤ ለሚያመጡ ድርጅቶች በሚወዳደሩበት ዘርፍ የራሳችሁ ምርት አምራች) መሆናችሁን የሚገልፅ መረጃ በማቅረብ በአመረታችሁት እቃ ላይ ብቻ የምትወዳደሩ መሆኑን እናሳውቃለን። ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ከታች ለተዘረዘሩት ሎቶች በተቋሙ ስም ሲፒኦ (CPO) በማሠራት ከዋናው ሰነድ ጋር ማያያዝ ይኖረባቸዋል።

ሎት1 ሎት2 ሎት3 ሎት4 ሎት5 ሎት6 ሎት7
0.5% 0.5% 0.5% 1% 2% 1% 7000
9000 6500 4500 20000 7000 1500 15000

ማሳሰቢያ

  • ተጫራቾች የተጫረቱበትን እቃዎች ናሙና/ሳምፕል/ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  • ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በገዙት ሰነድ የዋጋ ማቅረቢያ ቦታ ላይ ቫትን ጨምረው ስርዝ ድልዝ ሳይኖረው መሙላት አለባቸው፡፡
  • አሸናፊ ተጫራቾች ውል ከመፈረማቸው በፊት የውል ማስከበሪያ የተጫረቱበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% ማስያዝ አለባቸው፡
  • ብርሃን በር ቅድመ አንደኛ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት በጨረታው ከሚቀርቡት የእቃዎች ብዛት አሸናፊ ከሆነው ድርጅት እስከ 20% ድረስ መቀነስ ወይም መጨመር ይችላል።
  • ትምህርት ቤቱ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው፤
  • ተጫራቾች ያስገቡትን ሳምፕል ጨረታው ከተጠናቀቀ በኋላ በጊዜው ካልወሰዱ ለሚደርሰው ጉዳት ተቋሙ ተጠያቂ አይሆንም።

አድራሻ፡- አጠና ተራ ከተቃጠለው ሕንፃ ፊት ለፊት ስልክ ቁጥር 0112739672/0112792458

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአ/ከ/ከ/ከ በወረዳ 10 ብርሃን በር ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት

✨ messages.ai_summary
Birhan Ber Primary, First and Middle School in Addis Ababa is procuring various goods via open tender, split into 7 lots: uniforms (incl. tailoring), consumable office supplies, consumable educational materials, other consumables, printing, various books, and fixed assets. Bidders must have a renewed trade license, VAT registration, TIN, tax compliance, and be on the government supplier list.
Save Tender