የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ፣ በኢትዮጵያ ስካይላይት ሆቴል ስር የሚተዳደረው የአርባ ምንጭ ኮንፈረንስ ሪዞርት ውስጥ ለሦስት (3) ዓመታት የመሬት ገጽታ ጥገና አገልግሎት ለመስጠት ብቁ እና ልምድ ካላቸው የአገልግሎት አቅራቢ ድርጅቶችን በጨረታ አወዳድሮ ለማሠራት ይፈልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፡ SSNT-T640
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ፣ በኢትዮጵያ ስካይላይት ሆቴል ስር የሚተዳደረው የአርባ ምንጭ ኮንፈረንስ ሪዞርት ውስጥ ለሦስት (3) ዓመታት የመሬት ገጽታ ጥገና አገልግሎት ለመስጠት ብቁ እና ልምድ ካላቸው የአገልግሎት አቅራቢ ድርጅቶችን በጨረታ አወዳድሮ ለማሠራት ይፈልጋል።
ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ብቁ የሆኑ ድርጅቶችን ሥራውን ለማከናወን ጨረታውን እንዲሳተፉ ይጋብዛል።
የዘመኑን የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ በዘርፉ የታደሰ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣ የተጨማሪ እሴት ታከስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ በመንግሥት ጨረታዎች ለመሳተፍ ጊዜው ያላለፈበት ፈቃድ ያላቸው እና ከግብር እዳ ነጻ ስለመሆናቸው ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል።
ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት የሥራ ቀናት በአቅራቢያቸው ከሚገኝ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ የማይመለስ 200.00 ብር (ሁለት መቶ ብር) በሂሳብ ቁጥር 1000006958277(E-99) ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ጨረታ ቁጥር SSNT- T640 በሚል ገቢ በማድረግና የከፈሉበትን የገቢ ደረሰኝ ቅጅ (Deposit Slip Copy) ከታች በተጠቀሰው የኢሜይል አድራሻ በመላክ የጨረታ ሰነዱን ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ክፍል በኢሜይል ማግኘት ይችላሉ።
ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 50,000.00 / ሃምሳ ሺህ ብር / በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ወይም ለ150 ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ምንም አይነት ቅድመ ሁኔታ የሌለው የባንክ ዋስትና ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ከማንኛውም ኢንሹራንስ የሚቀርብ ዋስትና ተቀባይነት አይኖረውም፡፡ አሸናፊው ከተለየ በኋላ በጨረታው ለተሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ወዲያውኑ ተመላሽ ይሆናል።
ተጫራቾች በጨረታው ደንብ መሠረት የመጫረቻ ሠነዳቸውን (ቴክኒካልና ፋይናንሻል) ዋናውን እና ኮፒውን በኤንቨሎፕ አሽገው ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ክፍል ሐሙስ መስከረም 28 ቀን 2019 ዓ.ም እስከ ከረፋዱ 5:00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ አለባቸው፡፡ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት አዲስ አበባ ቦሌ በሚገኘው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና መሥሪያ ቤት የጨረታ መክፈቻ አዳራሽ ውስጥ በተመሳሳይ ቀን ከረፋዱ በ 5:30 ሰዓት ይከፈታል።
ለተጨማሪ ማብራሪያ፡- የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ክፍል
ስልክ ቁጥር 011-517-8025
ኢ-ሜይል: Eskedarya@ethiopianairlines.com
አየር መንገዱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
